የግብርና ዘርፉን ለማዘመን መንግሥት የግብርና ቴክኖሎጂዎችን የማስተዋወቅ ሥራ እየሠራ መኾኑን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

156

አዲስ አበባ፡ ሕዳር 27/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ያስመዘገበችውን የግብርና እድገት የሚያሳይ አውደ ርዕይ ተከፍቷል፡፡ በዝግጅቱ ላይ የግብርና ሚኒስትሩ ኡመር ሁሴንን ጨምሮ የክልልና የፌዴራል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በዝግጅቱ ላይ ተገኝተው እየጎበኙ ነው።

ዛሬ የሚካሄደው አውደ ርዕይ ነገ ለሚደረገው ቀጣይ መርሐ ግብር በር ከፋች መኾኑንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ዝግጅቱ የኢትዮጵያን የግብርና ጉዞ ለሚከታተለው የውጪው ማኅበረሰብ ማድረስ ዓላማ ያደረገ መኾኑም ተገልጿል።

አየለ መስፍን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleትኩረት የሚሹት የተጓተቱ የመሥኖ ፕሮጀክቶች።
Next articleመንግሥት በንፁሃን ላይ የሚደረግን ጥቃት እንዲያስቆም ፓርቲዎች ጠየቁ፡፡