ርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) በኢትዮጵያ ከጃፓን አምባሳደር ጋር ተወያዩ።

167
ባሕር ዳር: ሕዳር 05/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) በኢትዮጵያ ከጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።
ውይይታቸው በአማራ ክልል እየተካሄዱ ባሉ የልማት ሥራዎች ዙሪያ ነው። ርእሰ መስተዳድሩ በውይይታቸው ለአማራ ሕዝብ በአጠቃላይ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የጃፓን መንግሥት እያደረገ ላለው ሥራ አመስግነዋል።
በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ከርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ገልፀዋል።
የጃፓን መንግሥት በአማራ ክልል በንፁሕ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክ ላይ በሥፋት እየተሳተፈ መሆኑን ተናግረዋል።
የጃፓን መንግሥት በአማራ ክልል የካይዘን አተገባበር፣ ከባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ እየሠሩ መሆናቸውንም አስታውቀዋል። አምባሳደሯ በፎገራ የሩዝ ምርት ጥናት እያደረጉ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
የጃፓን መንግሥት በጦርነት ለተጎዱ ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ ማድረግ ከጀመረ መቆየቱን የገለፁት አምባሳደሯ እያደረገ ያለውን ድጋፍም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። የጃፓን መንግሥት በአማራ ክልል ትልልቅ ፕሮጄክቶች ላይ እየተሳተፈ መሆኑንም ተናግረዋል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበኩር ጋዜጣ – ሕዳር 05/2015 ዓ.ም ዕትም
Next articleበአሜሪካ ሀገር የሚኖሩ የጎንደርና የአከባቢው ተወላጆች በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ለቅዳሚት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የግብዓት ድጋፍ አደረጉ፡፡