
ባሕር ዳር፡ ሕዳር 02/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፎችን በተሻለ ሁኔታ ማቅረብን ጨምሮ አገልግሎቶች ዳግም እየጀመሩ መሆናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለጹ።
ማንኛውንም ሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብ የሚያስቸግር ምንም ዓይነት እንቅፋት እንደሌለ የገለጹት አምባሳደሩ ድጋፉ በክልሉ ከዚህ ቀድም ከነበረው በተሻለ ሁኔታ በሁሉም አካባቢዎች እንዲደርስ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
አምባሳደሩ በትዊተር ገጻቸው እንዳሰፈሩት 35 የእርዳታ እህል የጫኑ እንዲሁም 3 የህክምና ቁሳቁስ የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ሽሬ መድረሳቸውንም ጠቁመዋል።
በፓን አፍሪካኒዝም መንፈስና ጥበብ የተገኘው የሰላም ስምምነትና ውጤቱ አንዳንድ አካላትን ባያስደስትም በተፈጠረው እድል የአየር በረራዎች መፈቀዳቸውንና የተለያዩ አገልግሎቶችም እየተጀመሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ