የሰላም ስምምነት ሂደቱ በኬኒያ መካሄድ መቀጠሉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

184
አዲስ አበባ፡ ጥቅምት 30/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የመንግሥትና የሕወሃት ከፍተኛ ወታደራዊ መሪዎች በናይሮቢ እያደረጉ የሚገኙት ምክክር አሁንም መቀጠሉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም በሳምንታዊ መግለጫው ላይ አንዳሉት የተለያዩ ሀገራት ወዳጆቻችን በሰላም ስምምነቱ ላይ ያላቸውን ደስታ እየገለፁ ነው። ወዳጅ ሀገራት የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም እና የወደሙ ንበረቶችን ወደ አገልግሎት ለመመለስ ፍላጎታቸውን እያሳዩ ነው ብለዋል።
በስምመበቱ ላይ እንደተገለፀው መገናኛ ብዙኃኑ ስም ማጥፋትን እና ጦርነትን ማራገብን ትተው ሰላምን እና መረጋጋትን መዘገብ ይገባቸዋል ነው ያሉት። ለዚህ ደግሞ ሁሉም አስተዋፅኦ ማድረግ ይገባዋል ብለዋል።
በሌላ በኩል የዲፕሎማሲ ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በያዘው እቅድ መሰረት ከዋናው መሥሪያቤት እና ከሚሲዮኖች የመጡ የመሥሪያቤቱ ሠራተኞችን ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝ አንስተዋል።
ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው የሶማሊያ መንግስት በጠየቀው መሰረት 6 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና እና የመከላከያ ሚኒስቴር መሪዎች በተገኙበት ድጋፉ መሰጠቱን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቫርማ ሻክ ግብፅ እየተካሄደ በሚገኘው የአየር ንብረት ለውጥ ስኬታማ ቆይታ እያደረጉ መሆኑን ገልፀው ከጉባኤው ጎን ለጎን ከተለያዩ ሀገራት መሪዎች ጋር ውይየት እያደረጉ መሆኑንም ገልፀዋል።
በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ለኬኒያ የምታቀርበው የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ዝርጋታ መጠናቀቁን ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ለኬንያያ የምታቀርበው የ500 ኪሎ ቮልት ኤሌክትሪክ ኃይል የመስመር ዝርጋተው ሙሉ ለሙሉ መጠናቀቁን ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።
የኢትዮ-ኬኒያ የ500 ቮልት ኀይል ተሸካሚ መስመር ለረዥም ጊዜ ዝርጋታ ሲከናወን ቆይቶ በትናንትናው እለት የኀይል መስመር ሙከራ ተደርጓል። የፊታችን ህዳር ወር አጋማሽ ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ብለዋል።
ዘጋቢ፦ አንዱዓለም መናን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!!
Previous articleየጥበብ ሰው ሽኝት!
Next articleʺማይካድራ ትታወሳለች፣ ሳትረሳም ትታሰባለች”