“የአማራ መነሻ የኾነችውን ምድር ለማልማት ክልሉ በትኩረት ሊሠራ ይገባል” ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ

779
Made with LogoLicious Add Your Logo App

ሑመራ፡ ጥቅምት 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ከዞኖች ፣ ከከተማ አስተዳደሮች፣ ከአጋር አካላትና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ተግባራት የግምገማ መድረክ በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን በሑመራ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

በመርኃግብሩ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን ምክትል አሥተዳዳሪና የሰላምና ደኅንነት መምሪያ ኀላፊ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ፤ አንኳን ወደ አማራ መነሻ ወልቃይት ጠገዴ ምድር በሰላም መጣችሁ ብለዋል።

የወልቃይት ጠገዴ አማራ ሕዝብ ለበርካታ ዓመታት የመሰረተ ልማት ተጠቃሚ እንዳይኾን ሲሰራበት የነበር ሕዝብ በመኾኑ ከነጻነት ማግሥት ያለ በጀት የሚንቀሳቀስ ቢኾንም፤ ወልቃይት ቁጭትና እልህ በወለደቻቸው ልጆቿ ከኪሳቸው በማውጣት የተለያዩ መሠረተ ልማቶችን እያከናወነች ትገኛለች ።

የክልሉ የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ወደ አካባቢው በመምጣት ውይይት ማድረጉ የዞናችንን የመሠረተ ልማት ችግር ለመቅረፍ ያለውን ተነሳሽነት የሚያሳይ ነው ያሉት ምክክል አሥተዳዳሪው በትኩረት የተመለከታችሁትን የአማራ መነሻ መሬት ለማልማት በቁርጠኝነት ልትሠሩ ይገባል ብለዋል።

Made with LogoLicious Add Your Logo App

በመድረኩም የዞኖችና የከተማ አሥተዳደሮች የ2015 በጀት ዓመት 1ኛው የሩብ ዓመት የክንውን ተግባራትን እያቀረቡ ይገኛሉ። ተጨማሪ መረጃ የምናደርስ ይኾናል ።

ዘጋቢ፦ ያየህ ፈንቴ – ከሑመራ

ለሀገር ክብር በትግል እናብር‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

Previous article“የሞትነው እንደ ሀገር ነው፣ የተነሳነው እንደሀገር ነው፣ ትንሣዔያችን የጋራ ነው፣ ጥቅምት ሃይ አራትን ሁልጊዜም አንረሳውም” ኮሎኔል ተስፋዬ ኤፍሬም
Next articleበኩር ጋዜጣ – ጥቅምት 28/2015 ዓ.ም ዕትም