
ባሕር ዳር: ጥቅምት 22/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የሀገራዊ ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ የሚገኘውን ድርድር እንደማይቃወም አብን አስታውቋል። ይሁን እንጂ የአሸባሪውን ቡድን ትጥቅ ያስፈታና የቡድኑን ድርጅታዊ ኅልውና ባከሰመ መንገድ መሆን እንዳለበት ገልጿል።
እውን አሸባሪው ቡድን ሰላም ይፈልጋል? የሚለው ጉዳይ በአንክሮ ሊመረመር እንደሚገባ አስታውቋል።
“አብን ዛሬም ነገም የወከለውን የአማራ ሕዝብ ሰላምና ደኅንነት እንዲሁም ዘላቂ ጥቅም እንዲከበርና ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ ይሠራል፤ ይሄን ያማከለ የሰላም መድረክን አይቃወምም። ሆኖም ቡድኑ አሸባሪ እንጅ ሕጋዊ ባለመሆኑ ሊሠመርበት ይገባል” ብሏል።
ዘጋቢ:–በለጠ ታረቀኝ
ለሀገር ክብር በትግል እናብር!!