“የአሸባሪው ወያኔ ግፍ በጠለምት ነዋሪዎች ላይ …

378
Made with LogoLicious Add Your Logo App
ደባርቅ: ጥቅምት 22/2015 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው ወያኔ ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ በ27 ዓመታት የሥልጣን ዘመኑ በአማራ ሕዝብ ላይ የፈጸመው በደል አልበቃ ብሎት ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ጀምሮ በአማራ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት አድርሷል። ቡድኑ በሐምሌ ወር 2013 ዓ.ም በሰሜን ጎንደር ዞን በጠለምትና በአዳርቃይ ወረዳዎች ወረራ ከፈጸመ በኋላ በነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ግፍ ፈጽሟል።
“የደበቃችሁትን መሣሪያ አምጡ በማለት ዋሻ ውስጥ እጅና እግራችንን አስረው በዱላ፣ በሰደፍና በስለት በመደብደብና በመውጋት ግፍ ፈጽሞብናል” ብለዋል ነዋሪዎች።
አቶ አለሙ አበባው የአብርሃ አለሙና የአስፋው አለሙ አባት ናቸው። እንደ አቶ አለሙ ገለጻ “ልጆቼን ጫካ ውስጥ ደብቄ ልጆችህን አምጣ እያሉ በየጊዜው ያስሩኝ ነበር፤ ልጆቼ በጎረቤት ጥቆማ ከተያዙብኝ በኋላ እኔን ጨምሮ 9 ቤተሰቦቼ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ፈጽመውብኛል፤ የአካል ጉዳትም አድርሰዋል፤ ህይወትም አጥፍተዋል። ልጆቼን አካላቸውን በማጉደል ወልጄ እንዳልወለድኩ አድርገውኛል” ነው ያሉት።
አቶ አለሙ “የጠለምት ነዋሪ ኹሉ ‘አማራ ነህ’ እየተባለ ግድያ፣ እሥራትና ድብደባ ተፈጽሞበታል። ከሐምሌ ወር 2014 ዓ.ም ጀምሮ ሰራኮ በተባለችው ቀበሌ ከ40 በላይ ንጹሃን የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል” ብለዋል።
የሽብር ቡድኑ አካባቢውን ከለቀቀ በኋላ የወገን ጦር አባላት እንደተንከባከቧቸው ተጎጅዎች ገልጸዋል። በተፈጸመብን በደል ማዘን ብቻ ሳይኾን ቀለብ በመስጠትና ሕክምና አግኝተን ከጉዳታችን እንደምናገግም በመናገር ተስፋ ሰጥተውናል ብለዋል።
በአሸባሪው ወያኔ ከፍተኛ የአካል ጉዳትና የንብረት ዝርፊያ የተፈጸመባቸው እነዚህ ወገኖች መንግሥት የሕክምና እና የምግብ ድጋፍ እንዲያደርግላቸውም ጠይቀዋል።
ዘጋቢ፦ አድኖ ማርቆስ
ለሀገር ክብር በትግል እናብር!!
Previous articleዳያስፖራው ባለሀብት ለደብረ ታቦር ስፔሻላይዝድ አጠቃላይ ሆስፒታል የድንገተኛ ህክምና ክፍል ህንፃ ገንብተው ለማስረከብ የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ።
Next article“አፍሪካ ወደ ብልጽግና የምታደርገው ጉዞ አይቀሬ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ