ዳያስፖራው ባለሀብት ለደብረ ታቦር ስፔሻላይዝድ አጠቃላይ ሆስፒታል የድንገተኛ ህክምና ክፍል ህንፃ ገንብተው ለማስረከብ የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ።

127
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 22/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በካናዳ ነዋሪ የሆኑት ባለሀብቱ አቶ ማርቆስ ዘውዱ ለደብረታቦር ስፔሻላይዝድ አጠቃላይ ሆስፒታል የድንገተኛ ህክምና ክፍል ህንፃ ገንብተው ለማስረከብ የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ።
በግል ጉዳይ ወደ ደብረታቦር ስፔሻላይዝድ ሆስፒታሉ ባመሩበት ወቅት በተመለከቱት ችግር መነሻነት የግንባታ ሀሳቡን መጸነሳቸውን የሚገልጹት አቶ ማርቆስ፣ ድንገተኛ ክፍሉን ‘በደብረታቦር ሆስፒታል የአቶ ዘውዱ ተገኝ መታሰቢያ የድንገተኛ ክፍል’ በሚል ስያሜ በመገንባት ለማስረከብ ቃል ገብተዋል።
ግንብታው ሁለት የሀኪሞችና ሁለት የነርሶች ክፍልን ጨምሮ 30 የድንገተኛ አልጋዎች እንደሚኖሩት የተገለጸ ሲሆን፣ በስድስት ወራት ውስጥ ግንባታውን ለማጠናቀቅ ዕቅድ መያዙ ታውቋል።
ለግንባታው የመሰረት ድንጋይ በተቀመጠበት ወቅት የሆስፒታሉ የቦርድ ሰብሳቢና የደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ አቶ ይርጋ ሲሳይና ባለሀብቱ አቶ ማርቆስ ዘውዱ እንዲሁም የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት መገኘታቸውን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ መረጃ ያሳያል።
ለሀገር ክብር በትግል እናብር‼
Previous article“የባሕር ዳር ከተማን መዋቅራዊ ፕላን በማስጠበቅ ከተመዋን ውብና ለነዋሪዎቿ የምትመች ለማድረግ እንሠራለን” ዶክተር ድረስ ሳህሉ
Next article“የአሸባሪው ወያኔ ግፍ በጠለምት ነዋሪዎች ላይ …