የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ

211
ጥቅምት 14/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ቁልፍ የሚባሉ የትግራይ ከተሞችን መቆጣጠሩን ቀጥሏል።
ይህንን ሲያደርግም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በከተሞች ውጊያ ሳይደረግ የህወሓትን ወታደራዊ ዐቅም ለማሽመድመድ የሚያስችል ስልት ተጠቅሟል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ከሰብዓዊ የእርዳታ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ እየሠራ ይገኛል።
የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በእነዚህ አካባቢዎች አገልግሎት ለመጀመር የሚያስችል ዝግጅት እንዲያፋጥኑ እያደረገ ነው።
ከየአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር በመነጋገር ሕዝባዊ አሥተዳደር የሚቋቋምበትንና ማኅበራዊ አገልግሎቶች የሚጀምሩበትን መንገድ እያመቻቸ ይገኛል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአፍሪካ ኅብረት በኩል በደቡብ አፍሪካ በሚደረገው የሰላም ንግግር የሚሳተፍ ይሆናል።
አጋጣሚውንም የሰላም ንግግሩን ግጭቱን በሰላም ለመፍታት የሚቻልበት ዕድል አድርጎ ይመለከተዋል።
በመከላከያ ኃይላችን መስዋእትነት እየተስተካከለ የመጣውን ሁኔታ የበለጠ ለማጠናከር ምቹ አጋጣሚ የሚፈጥር አድርጎ ይወስደዋል።
በሰላም ንግግሩ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን ዛሬ ጠዋት ወደ ደቡብ አፍሪካ አምርቷል።
ጥቅምት 14/2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ለሀገር ክብር በትግል እናብር
Previous articleበኩር ጋዜጣ – ጥቅምት 14/2015 ዓ.ም ዕትም
Next article“የጥንካሬያችን ምንጭ ሕዝባችን ነው” የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት