አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን መንግሥት በአፍሪካ ህብረት በኩል በሚካሄደው የሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑን አስታወቁ።

281
ባሕር ዳር: ጥቅምት 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) መንግሥት በአፍሪካ ህብረት በኩል በሚካሄደው የሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሄራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አስታወቁ።
አምባሳደሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፥ የአፍሪካ ህብረት የሰላም ንግግሩ የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 14 በደቡብ አፍሪካ እንደሚካሄድ ማሳወቁን ጠቅሰዋል።
መንግሥትም በዚህ የሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑን ነው የገለጹት።
ሆኖም አሁንም መንግሥት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር የሚወስደውን የመከላከል እርምጃ ለማጠልሸት፣ የሀሰት ክስን ለመሰንዘርና የሰላም ሂደቱን ለማደናቀፍ በሚጥሩ አካላት ላይ የተሰማውን ቅሬታ ገልጸዋል።
ለሀገር ክብር በትግል እናብር!!
Previous articleአፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት መደረጉ በየትኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የለውም- የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
Next article