ኢትዮጵያ በአፍሪካ-ሕንድ የመከላከያ ኃይል ውይይት ላይ እየተሳተፈች ነው።

62
ባሕር ዳር: ጥቅምት 08/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብረሃም በላይ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በሕንድ ጉጃራት ግዛት ጋንዲናጋር ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ-ሕንድ የመከላከያ ኃይል ውይይት ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።
በውይይቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ዶክተር አብረሃም በላይ፣ እንደ አጠቃላይ የአፍሪካ-ሕንድ በተለይ ደግሞ የኢትዮጵያ-ሕንድ የመከላከያ ኃይል ትብብር ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል።
ውይይቱ በኢትዮጵያ እና ሕንድ መካከል ያለውን ወዳጅነት የበለጠ ለማጠናከር እና የመከላከያ ትብብራቸውን ለማጎልበት እንደሚረዳ ገልጸዋል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ እና ሕንድ የመከላከያ ኢንደስትሪ፣ የቴክኖሎጂ ልማት፣ የታጠቁ ኃይሎች አቅም ግንባታ፣ የጋራ ሥልጠና፣ የሳይበር መከላከያ፣ የማሪታይም ደኅንነት እና ፀረ-ሽብርተኝነትን ጨምሮ በጋራ ሊሠሩባቸው የሚችሉባቸው ዕድሎችን ለመፈተሽ መንገድ ይከፍታል ሲሉም አክለዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል የተከሰተውን ግጭት ለመፍታት እየወሰዳቸው ስላሉ ጥረቶችም ገለጻ አድርገዋል።
የሕንድ መንግሥት እና ሕዝብ ኢትዮጵያ ችግር ላይ በወደቀችበት ወቅት ላሳዩት አጋርነት የኢትዮጵያ መንግሥት ምስጋናውን እንደሚያቀርብም መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቋል።
የሕንድ መንግሥት ለእርሳቸው እና ለልዑካቸው ስላደረገው ግብዣ እና አቀባበልም ምስጋና አቅርበዋል።
ለሀገር ክብር በትግል እናብር!!
Previous article“ባለብዙው መክሊት ሀዲስ ዓለማየሁ!”
Next articleጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ!