
ባሕር ዳር: ጥቅምት 07/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ሀገራችን ኢትዮጵያ በዘመናት ሂደት ሰንደቅ ዓላማዋን አንግበው ለሉዓላዊነቷ እና ለአንድነቷ የተዋደቁ የጀግኖች ልጆች እናት ናት፡፡
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት 15ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በማስመልከት መግለጫ አውጥቷል፦
15ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ዛሬ በመላው ኢትዮጵያ ተከብሮ ይውላል፡፡ ቀኑን ስናከብር በደም ጠብቀን ያቆያናትን ሀገራችንን በደማችን እና በላባችን እያጸናን ነው፡፡ ሰንደቅ ዓላማ የሀገር ምልክት ነው። ይሄንን ዓርማ ይዘው ጀግኖች መሥዋዕትነት ከፍለዋል። በዓለም አደባባይ አሸንፈዋል። ይህ ሰንደቅ ዓላም ከልጅ እስከ ዐዋቂ ልብ ውስጥ የማይፋቅ ማኅተም አሳርፏል።
የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የትናንት የጋራ ታሪካችንን፤ የዛሬ ጥረታችንን እና የነገ ተስፋችንን እንዲሁምኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን አጣምሮ የያዘ የክብራችን እና የማንነታችን ማኅተም ነው፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ በዘመናት ሂደት ሰንደቅ ዓላማዋን አንግበው ለሉዓላዊነቷ እና ለአንድነቷ የተዋደቁየጀግኖች ልጆች እናት ናት፡፡ አሁን ባለንበት ዘመንምቢሆን ሰንደቅዓላማዋን አንግቦ፣ ኢትዮጵያን ሊያፈርሱ የተነሡ ጠላቶቿን አሳፍሮ የሚመልስ ትውልድ ያላት፣ የእልፍ ጥቁር አንበሶች ምድር ናት፡፡ የቅርብ እና የሩቅ ጠላቶቻችን ከሀገር ውስጥ ባንዳ አሸባሪዎች ጋር ተባብረው ኢትዮጵያን ለመበታተን መሄድ እስከሚችሉት ድረስ ተጉዘዋል፡፡ ሆኖም በልጆቿ ደምና ብርታት ምኞታቸዉ ቅዠት ሆኖ ቀርቷል፡፡
እኛ ካልመራናት ትፍረስ ብለው፣ በየአካባቢው ግጭት ጠንሰሰው፣ ጠብን ስፖንሰር አድረገው ሕዝባችንን ተስፋ ለማስቆረጥ ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም፡፡ እያንዳንዱ የሀገር ብተና ሤራቸው ተራ በተራ ሲከሽፍባቸው ደግሞ ሀገር ጠባቂ መከላከያ
ሠራዊታችንን በሌሊት አጥቅተው ጦርነት ከፍተውብናል። ይህ ሁሉ ወጥመድ ግን ለሰንደቃቸውክብር በሚሠዉጀግኖች የኢትዮጵያ ልጆች የጋራ ርብርብ ከግቡ ሳይደርስመክኖ ቀርቷል፡፡ በተለይም የሀገር መከላከያ ሠራዊታችን እና የክልል የጸጥታ ኃይሎች በሀገራችን ላይ ጦርነት የከፈቱ አሸባሪዎችን ድል ነሥተው፤ ሀገራቸውን ከመፍረስ ታድገዋል፡፡ በደማቸው ሰንደቅ ዓላማችንን አስከብረዋል፡፡
ጠላቶቻችን ጦርነት የከፈቱብን ሁሉንም ትኩረታችንን ወደ ጦር ግንባር አድርገን በሌሎች ዘርፎች ሽባ እንድንሆን አስበው ነበር፡፡ ዓላማቸው ኢትዮጵያን አዳክሞ ማፍረስ ነበር፡፡ ነገርግን ይህ ዓላማቸው በቁርጥ ቀን ልጆቿ ብርታትና እና በሕዝባችን ድጋፍ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡
“በደማችን እየጠበቅንበላባችን እናጸናለን” በሚል ዕሳቤ፤ የኢትዮጵያልጆች ከጫፍ እስከጫፍ በአንድ እጃቸው እያረሱ፤ በሌላኛው እጃቸው እየተኮሱ ሀገራቸውን እየገነቡ ነው። በአንድበኩል ከጠላት እየተከላከሉ፣ በሌላ በኩል የሰብል ምርታቸውን በብዙ እጥፍ አሳድገዋል፡፡
በዚህ ሂደትም ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ የግብርና ምርቶችን በማምረት፤ እንደ ሕዳሴ ግድብ ያሉ የተጀመሩ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን ወደላቀ ምዕራፍ በማድረስ እና ሌሎቹንም በማጠናቀቅ ሕዝባችንን ተስፋ ሊያስቆርጡ የተነሡ ጠላቶቿን ተስፋ አስቆርጣለች፡፡ በዚህም የሀገር ክብርና ሰንደቅ ዓላማችን ከፍ እንዲል ተደርጓል፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት የልማት ሥራዎችን እያጧጧፉ ጎን ለጎን የተከፈተባቸውን ጦርነት ሲመክቱ፤ ዐዋቂእና ወጣት አትሌቶቻችንደግሞበዓለምአደባባይ በሀገር ፍቅርስሜት ተናበው የሀገራቸውን አሸናፊነት ለወዳጅም ለጠላትም ዐውጀዋል፡፡ ሰንደቅ ዓላማችንን ከፍ
አድርገው አውለብልበዋል፡፡ ከሀገር አልፈው የአፍሪካ ኩራት ሆነዋል፡፡
ኢትዮጵያችን በብዙ ፈተና በተወጠረችበት በዚህ ወቅት ጠላቶቿን እየመከተች የልማት ሥራዎችን በታላቅ ስኬት ቀጥላበታለች፡፡ የምግብ ሉዓላዊነት ሳይኖር የሀገር ሉዓላዊነትን ማስከበር ከባድ ነው። በልመና ስንዴ የሰንደቅ ዓላማ ክብርን በዘላቂነት ማረጋገጥ አዳጋች ነው። ጀግኖቻችን በጦር ግንባር በደም ያስከበሯትን ሰንደቅ ዓላማ፤ በልማት ትግል በላባችን ከፍ ለማድረግ፣ ሁሉም በተሠማራበት መስክ የበኩሉን መወጣት ይኖርበታል፡፡
ጥቅምት 7 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ለሀገር ክብር በትግል እናብር!!