
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የሶማሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዛ አብዲ ባሬ በ10ኛው የጣና ፎረም ላይ ለመሳተፍ በዛሬው ዕለት ባሕር ዳር መግባታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
10ኛው የጣና ከዛሬ ጥቅምት 4 እስከ 6 ቀን 2015 ዓ.ም በባሕር ዳር የሚካሄድ መሆኑ ይታወቃል።
ለሀገር ክብር በትግል እናብር‼