መንግሥት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተፈጠረው ግጭት በሰላም እንዲፈታ ቁርጠኛ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ።

130

ጥቅምት 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ጋር ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።

  • አቶ ደመቀ ከልዩ መልዕክተኛው ማይክ ሐመር ጋር ባደረጉት ውይይት የኢትዮጵያ መንግሥት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተፈጠረው ግጭት በሰላም እንዲፈታ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።

ልዩ መልዕክተኛው በበኩላቸው አሜሪካ በአፍሪካ ሕብረት አደራዳሪነት ለሚካሄደው የሰላም ድርድር ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

በውይይታቸው ረጅም ዘመን ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ እና አሜሪካ የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ አጠናክሮ ለመቀጠል ተስማምተዋል።

ለሀገር ክብር በትግል እናብር‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

Previous articleየኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2022 የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ መሆኑ ተገለጸ።
Next articleኢትዮጵያዊነት ብዝኃነት፣ በነፃነት እንደተፈጠሩ በነፃነት መኖር፤ ለእሱም በኅብረት ዋጋ መክፈል እንደኾነ ርእሰ መስተዳድር ሀጅ አወል አርባ ተናገሩ፡፡