በሰሜን ሸዋ ዞን ሲያደብርና ዋዩ ወረዳ በኩታ ገጠም የተዘራ የስንዴ ሰብል ማሳ እየተጎበኘ ነው፡፡

246

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን ሲያደብርና ዋዩ ወረዳ በኩታ ገጠም የተዘራ የስንዴ ሰብል ማሳ እየተጎበኘ ነው፡፡

በወረዳው ኤጀርሶ እና ሮሜ ቀበሌዎች የተዘራ 150 ሄክታር የሰንዴ ሰብል ቁመና ነው ዛሬ እየተጎበኘ ያለው፡፡

ከዚህ ውስጥ በሮሜ ቀበሌ በኩታ ገጠም የተዘራውን 128 ሄክታር ሰብል የግብርና ሚኒስቴር፣ ፣የዞኑ እና የወረዳው የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች አሁን እየጎበኙ ይገኛሉ፡፡ ሰብላቸውን በኩታ ገጠም የዘሩ አርሦ አዳሮችም የሰብሉን ሁኔታ እና የተጠቀሟቸውን ግብዓቶች በተመለከተ ማብራሪያ እየሰጡ ነው፡፡

ዘጋቢ፡- ሀብታሙ ዳኛቸው

Previous article‹‹እኛ ከሌለን መንግሥት የለም እና እኛ ከሌለን ኢትዮጵያ የለችም የሚሉ ድምፆች ትክክል አይደሉም፡፡›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶክተር)
Next article“የሚያባሉን ሰዎች እድሜ ጠገብ ፖለቲከኞች ናቸው፤ ወጣቱ መንቃት አለበት፡፡” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶክተር)