
ባሕር ዳር: ጥቅምት 03/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በ10ኛው የጣና ፎረም ላይ ለመሳተፍ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ባሕር ዳር ገብተዋል።
የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ጨምሮን የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኅላፊዎች እና የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የሥራ ኅላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በአፍሪካ የጸጥታ እና ደኅንነት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚመክረው 10ኛው የጣና ፎረም ከነገ ጀምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀናት ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው
ለሀገር ክብር በትግል እናብር!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J