ለአካል ጉዳተኝነት እጅ ያልሰጠች የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ…

113

መስከረም 30/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ሀጃኢባ ያሲን ትባላለች። የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን እየወሰደች ነው።

የአካል ጉዳተኝነት ትምህርትን ጨምሮ ከማንኛውም ማኅበራዊ መስተጋብር እንደማያግድ ተማሪ ሀጃኢባን ማየት በቂ ነው።

ተነሳሽነት ካለ አካል ጉዳተኝነት ዓላማን ከማሳካት እንደማያግድ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን በእግሯ እየሠራች ያለችው ተማሪ ሀጃኢባ ጥሩ ማሳያም ጭምር ሆናለች።

የተማሪዋ ፈተናውን በእግሯ መሥራት አካል ጉዳተኝነት ተሰጥኦንና ተነሳሽነትን ከግብ ከማድረስ እንደማያግድም አመላካች ነው።

ተማሪ ሀጃኢባ አካል ጉዳተኝነት ግብን ለማሳካት ከመጣር እንደማያግድ ለበርካቶች ማስተማሪያ ሆናለች ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

ለሀገር ክብር በትግል እናብር‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

Previous articleበወልድያ እና ጎንደር ዩኒቨርሲቲዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ያለምንም ችግር መስጠት መጀመሩን ዩኒቨርስቲዎቹ ገለጹ።
Next articleአምባሳደር ስለሺ በሎስ አንጀለስ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና የአሜሪካ ባለሃብቶች ጋር ተወያዩ።