የጥበብ ሥራዎችን በክፍያ እና በማስታወቂያ አማራጮች መከታተል የሚያስችል “ሰዋሰው” የተሰኘ መተግበሪያ ሥራ ጀመረ።

161

መስከረም 30/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የጥበብ ሥራዎችን በክፍያ እና በማስታወቂያ አማራጮች መከታተል የሚያስችል “ሰዋሰው” የተሰኘ መተግበሪያ ተመርቆ ወደ ሥራ መግባቱን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።

መተግበሪያው የጥበብ አፍቃሪያን የጥበብ ሥራዎችን ካለ ክፍያ ከማስታወቂያ ጋር እና በክፍያ ካለ ማስታወቂያ መከታተል የሚያስችላቸው መሆኑ ተገልጿል። የሥነ-ጥበብ ሰዎች ከቅጂ እና ተዛማጅ መብቶች ጋር በተያያዘ የሚገጥማቸውን ችግርም የሚቀርፍ መሆኑም ተነግሮለታል።

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ.ር) የሰዋሰው መተግበሪያ ወደ ሥራ መግባት ኢትዮጵያ የያዘችውን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እና የግሉ ዘርፍ ተዋናይ እንዲሆን የተያዘውን ዕቅድ የሚደግፍ መሆኑን ተናግረዋል።

የክፍያ ሥርዓቱ ከቴሌ ብር እና እናት ባንክ ጋር መተሳሰሩ የሚደነቅ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፣ መተግበሪያው ዓለም አቀፍ መሆኑ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግም ያስችላል ብለዋል።

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሡ ጥላሁን በበኩላቸው፣ ከፍተኛ የሥራ ዕድል ይፈጥራል ተብሎ የተለየው አይ.ሲ.ቲ እና የጥበብ ዘርፍ ተቀናጅቶ ወደ ሥራ መግባቱ በሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

የጥበብ ሰዎች ከሥራዎቻቸው የሚገባቸውን እንዲያገኙ በማድረግ ዘርፉ እንዲነቃቃ ያደርጋል ተብሏል።

መተግበሪያው ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች እና የጥበብ ሰዎች በተገኙበት ተመርቆ ወደ ሥራ መግባቱን ከሚኒስቴሩ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

ለሀገር ክብር በትግል እናብር‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

Previous articleቺርቤዋ ሜስኬሩም 30 ጌርክ 2015 ም. አሜታ
Next articleበወልድያ እና ጎንደር ዩኒቨርሲቲዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ያለምንም ችግር መስጠት መጀመሩን ዩኒቨርስቲዎቹ ገለጹ።