
ሑመራ፡ መስከረም 29/2015 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪዉ ወያኔ ወደ ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ትንኮሳ ለመፈጸም የሚያደርገው ዳግም ሙከራ ለግብዓተ መሬቱ መፋጠን ጠቋሚ መሆኑን የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አሸተ ደምለው ገለጹ።
አሸባሪዉ ወያኔ በወልቃይት ጠገዴ የተለያዩ ግንባሮች ተደጋጋሚ ጥቃት ቢከፍትም አልተሳካለትም። አሁንም “የሕዝብ ማዕበል ተጠቅሜ ከቻልኩ ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራን እቆጣጠራለሁi፣ ካልቻልኩም ከሀገር እወጣለሁ” ፕሮፖጋንዳዉ ፈጽሞ ሊሳካለት እንደማይችል አመላክተዋል።
አሸባሪዉ ወያኔ ኢትዮጵያን ባስተዳደረበት ወቅት የወልቃይት ጠገዴን ህዝብ ስነ ልቦና ስለሚረዳ እና የመረረ ምትም እንደሚያሳርፍበት ስለሚያውቅ ፕሮፖጋንዳ ከመንዛት በዘለለ የተናገረውን ሊተገብር እንደማይችል አስተዳዳሪዉ ገልጸዋል። ሕዝቡ በአሸባሪዉ ወያኔ ላይ ያለው የመረረ ጥላቻ ወልቃይት ጠገዴን ረመጥ አድርጎታል ያሉት አስተዳዳሪዉ፣ ለአብነት በቅርቡ በምእራብ ግንባር ከ300 በላይ የሳምሪ ቡድን ወደ ወልቃይት ለመግባት ሙከራ ማድረጉንና ሁሉም ኀይሉ በገባበት ሳይወጣ መቅረቱን አስታውቀዋል።
አስተዳዳሪዉ እንደገለጹት የፖለቲካ አመራሩ፣ የፀጥታ አካሉ እና ህዝቡ በፕሮፖጋንዳ ሳይደናገር ጠላት በተዘጋጀበት ልክ በቂ ዝግጅት ተደርጓል። ሕዝቡም ለጥምር ጦሩ የኋላ ደጀንነቱን አጠናክሮ እንዲያስቀጥል፣ ከጥምር ጦሩ ጋር ተሰልፎ በግምባር እንዲፋለም፣ ወዳጅ መስለው ከኋላ ለጠላት መረጃ የሚያቀብሉ አካላትን ማጋለጡን እንዲቀጥል አሳስበዋል።
ዋና አስተዳዳሪዉ ፤ ወልቃይት ጠገዴ ጠላት በሚያወራው ልክ የጦርነት ቀጣና ሳይሆን አንጻራዊ ሰላም የሰፈነበት እና ከፍተኛ የልማት እንቅስቃሴ እየተከናወነበት ያለ ቀጣና መሆኑን ገልፀዋል። በመሆኑም ጠላት በፎከረዉ ልክ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ከጀመረ በቂ ሀይል የተዘጋጀለት በመሆኑ “ለሰብል ስብሰባ ጥሪ የተደረገላችሁ የቀን ሰራተኞች ያለምንም ስጋት ወደ አካባቢዉ መጥታችሁ ሕይወታችሁን እንድትመሩ” ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ፦ስማቸው አጥናፍ
ለሀገር ክብር በትግል እናብር‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J