“የመውሊድን በዓል የዓለምን ታሪክና የሰው ልጆችን ሕይወት በመለወጥ ማክበር ይገባል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

115

ባሕር ዳር: መስከረም 28/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመውሊድን በዓል የዓለምን ታሪክና የሰው ልጆችን ሕይወት በመለወጥ ማክበር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም በነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ) መወለድ ዓለም እጅግ ተጠቅማለች፤ የዓለምን ታሪክም ቀይረዋል ብለዋል።

እንዲሁም የሰው ልጆችን ሕይወት ለውጠዋል ነው ያሉት።

የመውሊድን በዓል የምናከብረው የዓለምን ታሪክና የሰው ልጆችን ሕይወት በመለወጥ መሆን አለበትም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።

በግብርና እና በአምራች ኢንዱስትሪው ላይ እየሠራን ያለው ሥራ የሀገራችንን ታሪክና የሕዝባችንን ሕይወት የሚለውጥ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ኢትዮጵያን ከጦርነት በመገላገል ፊታችንን ሙሉ በሙሉ ታሪክና ሕይወት ወደሚለውጡ ዕቅዶቻችን እንዞራለን ብለዋል።

የተጀመረው “የሌማት ትሩፋት” የቤተሰቦቻችንን ሥርዓተ ምግብ እንዲለውጥ ተግተን እንስራ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

ለሀገር ክብር በትግል እናብር!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

Previous articleነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዓ.ወ) ከውልደታቸው እስከ ህልፈታቸው ያልተለየችው በረካ
Next articleወልቃይት ጠገዴ ከፍተኛ የልማት እንቅስቃሴ ያለበት አካባቢ ነው – የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አሸተ ደምለው