ነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዓ.ወ) ከውልደታቸው እስከ ህልፈታቸው ያልተለየችው በረካ

346

ባሕር ዳር: መስከረም 28/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በረካ በነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ.) አባት አብዱሏህ ቤት ውስጥ ብቸኛዋ አገልጋይ ነበረች።

አብዱሏህ ለንግድ በሄዱበት መሞታቸው ተሰማ፡፡

የነብዩ እናት የባለቤቷን ሞት ከሰማች ጊዜ ጀምሮ እስክትወልድ በረካ አልተለየቻትም ነበር፡፡

ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዓ.ወ) ሲወለዱ በመጀመሪያ ያቀፏቸው የበረካ እጆች ነበሩ፡፡

ነብዩ (ሰ.ዓ.ወ) ስድስት ዓመት ሲሞላቸው እናታቸው አሚና በየስሪብ የሚገኘውን የነብዩ አባትን መቃብር በጎበኘች ጊዜ በፀና ታመመች፡፡

በየስሪብ እና በመካ መካከል አል-አብዋ ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ ህመሙ ስለፀናባት በሚተናነቅ ድምፅ “በረካ ሆይ! በቅርቡ ይህን ዓለም እለያለሁ፤ ልጄን ሙሐመድ (ሰ.ዓ.ወ) ተንከባከቢው፤ በሆዴ ውስጥ እያለ አባቱን አጣ፤ አሁን ደግሞ እናቱን ሊያጣ ነው፡፡ አንች እናት ሁኝው፤ አትተይው” በማለት ለበረካ አደራ አለቻት። በረካም አምርራ አለቀሰች።

በረካ ነብዩን (ሰ.ዓ.ወ) ይዛ ወደ መካ አያታቸው አብዱል ሙጦሊብ ቤት ተመለሰች፡፡

ነብዩ ስምንት ዓመት ከሁለት ወር ሲሆናቸው አያታቸው አብዱል ሙጦሊብ ስለሞቱ ነብዩን ይዛ ወደ አጎታቸው አቡጧሊብ ሄደች።

ነብዩ (ሰ.ዓ.ወ) እስኪያድጉና እስኪያገቡ ድረስ ተንከባክባ፣ ፍላጎታቸውን አሟልታ አሳደገቻቸው፡፡

ከዚያም ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዓ.ወ) ኸድጃን አግብተው በረካ አብራ መኖር ጀመረች።

ነብዩ (ሰ.ዓ.ወ) ወደ መዲና ሲሰደዱ በረካ ቤታቸውን እንድትቆጣጠር መካ ትተዋት ሄዱ። ነገር ግን ለነብዩ (ሰ.ዓ.ወ) በነበራት ጥልቅ ፍቅር ምክንያት በዛ በረሃማና ተራራማ መሬት፣ ረጅምና አስቸጋሪ መንገድ በእግሯ ተጉዛ ወደ መዲና ተሰዳለች።

በረካ ይህን ዓለም የተሰናበተችው በኸሊፋው ኡስማን ዘመን ነበር፡፡

ምንጭ፡- ኢትዮሙስሊምስ ዶት ኔት፣ አፍሪካ ቲቪ፣ ዛውያ ቲቪ

በእመቤት አሕመድ

ለሀገር ክብር በትግል እናብር!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

Previous articleየርእሰ መሥተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ የመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!
Next article“የመውሊድን በዓል የዓለምን ታሪክና የሰው ልጆችን ሕይወት በመለወጥ ማክበር ይገባል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ