የርእሰ መሥተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ የመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!

221

ባሕር ዳር፡ መስከረም 28/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ለመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የመልዕክቱ ሙሉ ቃል፦

እንኳን ለመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

መውሊድ የታላቁ የእስልምና ነቢይ የነብዩ ሙሐመድ የልደት በዓል ነው፡፡ ከመውሊድም ሰላምን፣ ፍቅርን፣ ትግስትን፣ አንድነትን እንማራለን።

መውሊድ መተባበርና አብሮነት፤ መተዛዘንና መፈቃቀድ በተግባር የሚገለጽበት ነው። ያለው ለሌለው የሚያካፍልበት፣ ማህበራዊ ትስስሩን የሚጠናከርበት፤ በአንድ አብሮ የሚያሳልፍበት በዓል ነው።

በመሆኑም ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር የነብዩ መሐመድን መልካም አስተምህሮቶች ለትዉልዱ በማስተላለፍ ፣ የተቸገሩትን በማሰብ፣ በመረዳዳትና በመደጋገፍ ሊሆን ይገባል።

ስለሆነም እንኳን ለ1ሺህ 497ኛው የነብዩ መሐመድ መውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን እያልኩ፦ በዓሉ የሰላም፣ የደስታ፣ የአብሮነትና አንድነት እንዲሆን በራሴና በክልሉ መንግሥት ስም እመኛለሁ።

መልካም በዓል!
ዒድ-ሙባረክ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ልጆቿን ይባርክ!

ለሀገር ክብር በትግል እናብር‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

Previous article“ዘረኝነት መጥፎ ሽታ ያለው ነገር ነውና ራቁት”
Next articleነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዓ.ወ) ከውልደታቸው እስከ ህልፈታቸው ያልተለየችው በረካ