
መስከረም 27/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የመወሊድ በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 1 ሺህ 497ኛውን የነብዩ መሐመድ የመወሊድ በዓልን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
የዘንድሮ የመወሊድ በዓል ነብዩ መሐመድ ለመላው ዓለም የተላኩ በመኾናቸው የሳቸውን ልህቀት በሚገልጽ መልኩ “የእዝነቱ ነብይ” በሚል መሪ ሐሳብ እንደሚከበር ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ ሁሉም የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የነብዩ መሐመድ ፈለግን መከተል ግዴታ እንደኾነ ገልጸዋል፡፡ ሕዝበ ሙስሊሙ በሀገሪቱ ሰላም እንዲወርድ፣ አቅመ ደካሞችንና የተፈናቀሉ ወገኖችን በመርዳት በዓሉን ማክበር እንዳለበት ፕሬዚዳንቱ አስገንዝበዋል፡፡
ምዕመናኑ ለሰላም በመሥራት ከመንግሥት ጎን መቆም አለበት ብለዋል፡፡
ለሀገር ክብር በትግል እናብር

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ