”ጧሪም ቀባሪም ልጄን ቀሙኝ” በቆቦ ከተማ ልጃቸው በአሸባሪው የሕወሓት ቡድን የተገደለባቸው እናት

168
Made with LogoLicious Add Your Logo App
ወልድያ: መስከረም 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ወይዘሮ ጥሩየ ቸኮል ይባላሉ። የቆቦ ከተማ ነዋሪ ናቸው። ጉልበታቸው ሳለ ጠላ በመሸጥ በሚያገኙት አነስተኛ ገቢ ልጆቻቸውን አሳድገው ለቁም ነገር አብቅተዋል። ዛሬ እድሜያቸው እየገፋ ሲመጣ አቅማቸው ሲደክም አብሯቸው የነበረው ልጃቸው እየረዳቸው ኑሮን እየገፉ ነበር፡፡
ይሁን እንጅ ሠርቶ የሚያበላቸው ጡሮ ይቀብረኛል ብለው የሚያስቡትን የ25 ዓመት ለጋ ወጣት ልጃቸውን አሽባሪው የሕወሓት ቡድን በግፍ ገድሎባቸዋል፡፡ ሐዘኑ መሪሪ ኾኖባቸዋል፤ የወደፊት ተስፋቸውን አሸባሪ ቡድኑ አጨልሞባቸዋል፡፡
“ጧሪም ቀባሪም ልጄን ቀሙኝ” ብለዋል ወይዘሮ ጥሩየ።
የሟች ታላቅ ወንድም መምህር ንጉሥ ተገኑ እንዳሉት ሟች ለእናቱ ቅን ታዛዥ፣ ለሰዎች በጎ አሳቢ፣ ሠርቶ ለመለወጥ ሁልጊዜ የሚታትር ምሥጉን ልጅ መኾኑን ነው የተናገሩት፡፡
የአሸባሪ ቡድኑ አባላት በየሰፈሩ ድብደባ እና ዘረፋ ሲፈጽሙ ነበር፤ ወንድሜ ግን እንደነሱ ሲዘርፍ እና አጸያፊ ተግባር ሲፈጽም ሳይኾን ጎረቤቶቹን ከአሸባሪዎቹ ዘረፋና ድብደባ ለማዳን ሲል አረመኔዎቹ የጭካኔ በትራቸውን አሳረፉበት ይላል መምህር ንጉሥ፡፡
“የእኛን ወንድም ብቻ ሳይኾን የአሸባሪ ቡድኑ አባላት ንጹሐንን ገድለዋል፤ በርካታ ሴቶችን ደፍረዋል፤ ሀብትና ንብረት ዘርፈዋል፤ አውድመዋል ብለዋል፡፡
መምህር ንጉሥ፥ አሸባሪው ቡድን እስከመጨረሻው እንዲጠፋ መረባረብ ይገባል ነው ያሉት።
ዘጋቢ፡- ባለ ዓለምዬ
ለሀገር ክብር በትግል እናብር
Previous articleየአፍሪካ ኅብረት የሰላም ንግግሩን የሚመሩ አካላትን፤ ቀንና ስፍራን አሳውቆ የሰላም ውይይቱ እንዲጀመር ይፋዊ ጥሪ ማቅረቡን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
Next article❝እጄን ጠላት ከሚነካት፣ ተከዜ ነብሴን ይውሰዳት❞