በአማራ ክልል በጦርነት ምክንያት የደረሰውን ሰብዓዊ ቁሳዊና ስነ ልቦናዊ ጉዳትና ውድመት የሚያሳይ ውብሳይት ተበለፀገ።

584

አዲስ አበባ፡ መስከረም 19/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ከሰኔ 2013 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 2014 ዓ.ም ያለውን ጉዳት ሚያሳይ ዌብሳይት በልጽጎ ይፋ ሆኗል።

በጥምረት ጥናትና ምርምር ያደረጉት በአማራ ክልል በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎች መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፈንድ ጽሕፈት ቤት፣ የአማራ ምሁራን መማክርት እና የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም የተለያዩ ግኝቶችን ይዘው ይፋ አድርገዋል። ዝርዝሩን ይዪ፦
https://www.facebook.com/118697174971952/posts/1920334038141581/

በጥናት ውጤቱ የተደረሰበት ግኝትና በሕዝቡ ላይ የደረሰውን ሁለንተናዊ ጥቃትና ውድመት ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተደራሽ እንዲሆን የጥናቱ አዘጋጆች በመጽሐፍ ሰንደዋል፤ ዌብሳይት አበልፅገዋል።


በዌብሳይቱም በዕያንዳንዱ ቦታና ጥናቱ ባካተተው ጊዜ ውስጥ የተፈፀሙ ጥቃቶችንና የደረሱ ሁለንተናዊ ጉዳቶችን በቦታና በጊዜ የለየና የምስል፣ የድምፅና የተለያዩ ጥንቅሮችን ባቀፈ መልኩ የተዘጋጀ ሆኖ ሁሉም ባለበት ቦታ ሆኖ ተደራሽ እንዲሆን ተዘጋጅቷል ብለዋል
በአማራ ክልል በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎች መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፈንድ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር አባተ ጌታሁን።

በዌብሳይቱ በጥናቱ ያልተካተቱና አሁንም በወረራ የተያዙ አካባቢዎችን ሁለንተናዊ ጉዳቶች እየተጠኑ እንደሚካተቱ ተጠቁሟል።

ዘጋቢ፦ እንዳልካቸው አባቡ

ለሀገር ክብር በትግል እናብር‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

Previous articleበአሸባሪው ሕወሃት ወረራ በአማራ ክልል የደረሰው ጉዳት በጥናት የተገኘው ውጤት ይፋ ሆነ።
Next articleየብፁዕ አቡነ በርናባስ ጥሪ…