ባሕርዳር ጣና ፎረምን ለማስተናገድ ዝግጅቷን አጠናቃለች!

118
ባሕር ዳር፡ መስከረም 18/2015 ዓ.ም (አሚኮ) አፍሪካዊያንን ያስተሳሰረው ጣና ፎረም ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ በአፍሪካ አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ መፍትሄ ለማፈላለግ የተዋቀረ ነፃ ተቋም ነው፡፡
በመጭው ጥቅምት ወር መጀመሪያ አፍሪካውያን ስለ አህጉራዊ ጉዳዮቻቸው ሊመክሩ ከዓባይ ዳር፣ ከጣናዋ እልፍኝ ባሕር ዳር ላይ ቀጠሯቸውን አድርገዋል፡፡
በቀጠሯቸው መሠረት ከ 250 በላይ አፍሪካውያን ጥቅምት ከ04 አስከ 06/2015 ዓ.ም ተገናኝተው ይመክራሉ፡፡
ፎረሙ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት ፣ የሳይንስ እና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ባሕር ዳርን ከአፍሪካ ከተሞች መርጦ ብቸኛዋ የትምህርት ከተማ አድርጎ በሰየማት የአፍሪካ ምርጧ እና ፅዱዋ ከተማ ባሕር ዳር ይካሄዳል።
ጣና ሐይቅን እና ዓባይን ተንተርሳ የበቀለችው የዘንባባ ንግስት ባሕር ዳር ጣና ፎረምን ለማስተናገድ ዝግጅቷን አጠናቃላች ሲል የከተማዋ አሥተዳደር አስታውቋል።
ለሀገር ክብር በትግል እናብር‼
Previous articleቺርቤዋ ሜስኬሩም 15/2015 ም.አሜታ እትሜት
Next articleMaxxansa Gaazexaa Hirkoo Fulbaana 15/2015