የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የአሸናፊነት መንፈስ ከተቀበረበት ወጥቷል፤ ከእንግዲህ እንደ ችቦ እያበራ ይቀጥላል እንጂ ማን ያቆመዋል!

233

የብሔራዊ መረጃና ደሕንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል ተመስገን ጥሩነህ

ባሕር ዳር: መስከረም 16/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የብሔራዊ መረጃና ደሕንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል ተመስገን ጥሩነህ ለብርሃነ መስቀሉ የእንኳን
አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

የመስቀል በዓል፣ በክፉዎች ምኞትና ጥረት የሚያልቅና የሚያበቃ ነገር እንደሌለ የተማርንበት ነው። መስቀሉን ሰውረው የቀበሩት ሰዎች፣ የመስቀሉ ነገር በእነርሱ አሸናፊነት ያለቀ፣ የተጠናቀቀ መስሏቸው ነበር። ታሪክ ሠሪ ሰውና ታሪካዊ ጊዜ እስኪመጣ ድረስ እውነትም ያለቀ መስሎ ነበር።

ንግሥት ዕሌኒ የምትባል ታሪክ ሠሪና ነገሮች የተለወጡበት ታሪካዊ ጊዜ መጣ። መስቀሉም ከተቀበረበት ወጣ። ታሪክም ተለወጠ።

የክፉዎች ታሪክ እየተለወጠ ነው። ታሪክ እናድርጋት ያሏት ኢትዮጵያ ታሪክ እያደረገቻቸው ነው። የኢትዮጵያ ጉዞ በክፉዎች ድል አድራጊነት ሊጠናቀቅ እንደማይችል እየታየ ነው። ታሪክ ሠሪ ጀግኖችና ታሪካዊ ጊዜ ገጥሟል። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የአሸናፊነት መንፈስ ከተቀበረበት ወጥቷል። ከእንግዲህ እንደ ችቦ እያበራ ይቀጥላል እንጂ ማን ያቆመዋል! ብለዋል አቶ ተመስገን በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክታቸው።

ለሀገር ክብር በትግል እናብር‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

Previous articleበኩር ጋዜጣ – መስከረም 16/2015 ዓ.ም ዕትም
Next article❝መስቀል የብሩህ ተስፋ፣ የብርሃንና የድል ምልክት ነው ፤ ደመራም የአንድነት እና የሕብረት ተምሳሌት ነው❞ ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)