
ባሕር ዳር፡ መስከረም 11/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ያወጣው ሪፖርት ለፖለቲካዊ ፍላጎት ማስፈጸሚያነት የዋለ እና እውነታውን የካደ መሆኑን የታሪክ ተመራማሪው ጄፍ ፒርስ አስታውቀዋል።
ጄፍ ፒርስ ካናዳዊው የታሪክ ተመራማሪ እና ደራሲ ሲሆኑ በዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የምርመራ ግኝት ላይ ሐሳባቸውን አጋርተዋል፡፡
ጄፍ ፒርስ በኮሚሽኑ በምስክርነት እና በመረጃ ምንጭነት የተጋበዙ ሰዎችን ጠቅሰው በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ÷ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ተፈጽሟል ተብሎ በኮሚሽኑ የቀረበው ሪፖርት ለሽብር ቡድኑ ያደላ እና ኮሚሽኑ የጋበዛቸው የመረጃ ምንጮቹ ላይም መደናገርን የፈጠረ እንደሆነ አስፍረዋል፡፡
ለሀገር ክብር በትግል እናብር