
ባሕር ዳር፡ መስከረም 11/ 2015 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው ሕወሃት ከምስረታው ጀምሮ አላማው ከጠላቶች ጋር በማበር የኢትዮጵያን ኅልውና በማዳከም መጨረሻም ማፍረስ መሆኑን አቶ ሙዑዝ ገብረህይወትና ጋዜጠኛ ፍሬዘር ነጋሽ ገልጸዋል።
“አሸባሪው ሕወሃት አጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብና በተለይም የትግራይ ክልል ሕዝብ ጠላት በመሆኑ ሀገርን ከጥፋት ለመታደግ በጋራ መቆም ይገባል” ብለዋል።
አሸባሪ ቡድኑ ከጥንትም የሕዝቦችን በሰላም መኖር የማይሻ፤ ያለ ግጭት ኅልውና የሌለው መሆኑን አስታውሰው አሁንም በዚሁ ተግባሩ ቀጥሎበታል ነው ያሉት።
የኢትዮጵያን ኅልውና ለማጥፋት በማሰብ ባዘጋጀው ሰነድ ላይ በግልጽ የተቀመጠው ጽሁፍም ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከአሸባሪዎቹ አልሸባብና ከሸኔ ጋር እንደሚሠራ አመላክቷል፡፡
“በስልጣን ዘመኑ ሞክሮ ያልተሳካለትን ኢትዮጵያን የመበታተን ዓላማው ዛሬ ለታሪካዊ ጠላቶች ፈረስ በመሆን ጭምር እኩይ ሃሳቡን ለማሳካት እየሰራ ይገኛል” ነው ያሉት አቶ ሙኡዝ፡፡
አሸባሪው ቡድን ከውጭ ከአሸባሪው አል-ሸባብና ሌሎች የጥፋት ቡድኖች ጋር በመሆን ኢትዮጵያን ለማፍረስ አሁንም በጥረት ላይ ይገኛል ብለዋል።
በ1969 ዓ.ም ከሶማሌ ጦር ጋር በመሆን ኢትዮጵያን ወግቶ እንደነበር ያሥታወሱት አቶ ሙዑዝ፤ በቅርቡም ከአሸባሪው አልሸባብ ጋር በመተባበር ታሪካዊ ስህተቱን ደግሞታል ነው ያሉት።
በተለያዩ አካባቢዎች ሶስተኛ ዙር ጦርነት በመክፈት የመንግስትን የሰላም አማራጭ እንደማይቀበለው በግልጽ በማሳየት በጥፋቱ ቀጥሏል ብለዋል።

ጋዜጠኛ ፍሬዘር ነጋሽ በበኩሏ የሕዝብ ሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብት መከበር ጉዳይ የማያሳስበው አሸባሪው ሕወሃት፤ ለትግራይ ክልልም ሆነ ለመላው ኢትዮጵያ ዘላለማዊ ጠላት መሆኑን ገልፃለች።
የኢትዮጵያን ውደቀት ከሚመኙ ኀይሎችና አማጽያን ጋር በማበር ኢትዮጵያን ለማፍረስ መሻትም የቡድኑ መሰረታዊ ባህሪ መሆኑን ትናግራለች።
አሸባሪው ሕወሃት በትግራይ ክልል ሕዝብ ስም ሲነግድ ኖሮ አሁንም በተመሳሳይ ተግባሩ ቀጥሎ ብዙ መከራና ስቃይ እያስከተለ መሆኑን ተናግረዋል።
በተለይም የትግራይ ክልል ሕዝብ አሸባሪ ቡድኑ ወደ ሰላማዊ ውይይት እንዲመጣ ጫና መፍጠር ከዚህ ካለፈም የህግ ተጠያቂ ማድረግና በእንቢተኝነቱ ከቀጠለም ሊዋጉት ይገባል ነው ያሉት።
ኢዜአ እንደዘገበው፤ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች አሸባሪዎቹን ሕወሃትና ሸኔ እንዲሁም ሌሎች የጥፋት ቡድኖችን በማስተባበር ሀገር ለማፍረስ እየሠሩ በመሆኑ ለኢትዮጵያ ኅልውና ስንል ሁላችንም በጋራ መቆም ይጠበቅብናል ብለዋል።
ለሀገር ክብር በትግል እናብር
