
ባሕር ዳር: መስከረም 11/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት እንደማትቀበለው በጀኔቭ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ዘነበ ከበደ አስታወቁ።
ሪፖርቱን በተመለከተ ለፈረንሳዩ የዜን ወኪል አዣንስ ፍራንስ ፕረስ የተናገሩት በጀኔቭ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ዘነበ ከበደ፣ ሪፖርቱን ያወጣው ኮሚሽን መንግሥት ርሃብን በጦር መሳሪያነት ስለመጠቀሙ አንድም ማስረጃ አላቀረበም ብለዋል።
አምባሳደር ዘነበ በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በኢትዮጵያ ስለተፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተመለከተ ኮሚሽኑ ያወጣው ሪፖርት አስቀድሞ የታቀደ እና ፖለቲካዊ ዓላማ ያለው መሆኑን ገልፀዋል።
ኤክስፐርቶቹ የመጀመሪያ ግኝት ብለው ያወጡት ሪፖርት ለምርመራ ወደ ክልሎቹ በእግራቸው ሳይረግጡ ያወጡት መሆኑ እና የሪፖርቱ ድምዳሜዎችም እርስ በርስ የሚጋጩ እና አድሏዊ ናቸው ሲሉ አምባሳደሩ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ለሀገር ክብር በትግል እናብር!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ