ዘመነ ካሴ በሕግ ቁጥጥር ሥር ዋለ።

1330

ባሕር ዳር፡ መስከም 11/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን የታክቲክ ምርመራ ምክትል ዘርፍ ኀላፊ ኮማንደር ክንዱ ወንዴ በሰጡት መግለጫ፤ ዘመነ ካሴ በኅብረተሰቡ ጥቆማ በሕግ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተካሔደበት ነው ብለዋል።

በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 03 ከግለሰብ ቤት መያዙን ገልጸዋል።

የወንጀል ተጠርጣሪው በሕግ ቁጥጥር ሲውል 541 ሺህ ብር እና ከሌሎች ኤግዚቢቶች ጋር መያዙን ተናግረዋል።

ምርመራው የሚካሔደው በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መሆኑን አረጋግጠዋል።

ኮማንደር ክንዱ ተጠርጣሪው በሕግ ሲፈለግ እንደቆየ ገልጸው እንዲያዝ ለተባበረው ማኅበረሰብ ምስጋና አቅርበዋል።

ማንም ከሕግ ማምለጥ እንደማይችል የተጠርጣሪው መያዝ ማሳያ ነው ብለዋል።

ለሀገር ክብር በትግል እናብር‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

Previous article“ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ኢትዮጵያን ለማዳከምና ለማጠልሸት የፖለቲካ ተልዕኮ የተሰጠው አካል ነው” አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን
Next article“አሸባሪው ሕወሃት የተቃርኖ ሃሳብ የሚያራምድን ሁሉ ማጥፋት ከምስረታው ጀምሮ የሚከተለው ስልት ነው” አረጋዊ በርሄ (ዶ.ር)