
ባሕር ዳር: መስከረም 07/2015 ዓ.ም (አሚኮ) አዲሱ ሀገራዊ ሥርዓተ ትምህርት በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ሙሉ ለሙሉ፤ ከ9 እስከ 10ኛ ክፍል ደግሞ በተመረጡ ትምህርት ቤቶች የሙከራ ትግበራ የሚደረግ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ መስከረም ዘጠኝ በሀገር አቀፍ ደረጃ ትምህርት እንደሚጀመርም ተጠቁሟል፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርቶች ሥርዓተ ትምህርት ዴስክ ኃላፊ ወይዘሮ ዛፉ አብርሃ በሥርዓተ ትምህርት አተገባበሩና ትምህርት ስለሚጀመርበት ሁኔታ ላይ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ ላለፉት አምስት ዓመታት ሲጠና የቆየው አዲሱ ሀገራዊ ስርዓተ ትምህርት በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተግባራዊ ይደረጋል። ይህ ሥርዓተ ትምህርት ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ሙሉ የሚተገበር ሲሆን ከ9ኛ እስከ 10ኛ ክፍል ደግሞ የሙከራ ትግበራ ይደረጋል። 11ኛ እና 12ኛ ክፍል የነባሩ ሥርዓተ ትምህርት እስከ 2016 ዓ.ም ድረስ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ስርዓተ ትምህርቱ በዚህ ዓመት ሙሉ እና የሙከራ ትግበራ ከተደረገበት በኋላ በ2016 ዓ.ም የሚኖሩ ችግሮችን በማስተካከል እና በማዳበር ሙሉ ለሙሉ ወደ ትግበራ የሚገባ መሆኑን ጠቁመው፤ አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ባሉ የግልም ሆኑ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች የሚተገበር መሆኑን አስታውቀዋል። ዘገባው የኢፕድ ነው
ለሀገር ክብር በትግል እናብር!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J