ጣና ፎረም በመጭው ጥቅምት ወር አጋማሽ በባሕር ዳር ከተማ ይካሄዳል።

112

ባሕር ዳር: መስከረም 06/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የ2015 ዓ.ም ጣና ፎረም ጉባኤ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን አስመልክቶ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ከጣና ፎረም አዘጋጅ ኮሚቴ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሣኅሉ (ዶ.ር) እና ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ጣና ፎረም ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ በአፍሪካ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መፍትሔ ለማፈላለግ የተቋቋመ አፍሪካዊ ተቋም ነው፡፡

የአፍሪካ መሪዎች በአፍሪካ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረው አቅጣጫ የሚያስቀምጡበት ጣና ፎረም በየዓመቱ በባሕር ዳር ከተማ የሚካሄድ ሲኾን በአፍሪካ ኢኮኖሚ፣ ሰላም፣ ንግድ ትስስር እና የተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀም ዙሪያ ይመክራል፡፡

በመጭው ጥቅምት ወር አጋማሽም ከ250 በላይ የሚኾኑ አፍሪካውያን የፎረሙ ተሳታፊዎች ስለ አህጉራዊ ጉዳዮቻቸው ተገናኝተው ለ12ኛ ጊዜ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ለሀገር ክብር በትግል እናብር‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

Previous article“የጀግና ልጆች፣ የጠረፍ አጥሮች”
Next articleየአሸባሪው ሕወሓት ቡድን በሰቆጣ ዙሪያ ወረዳ ሐሙሲት ቀበሌ የሚገኘውን ታጋይ ሰርክዓለም ትዛዙ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤትን አወደመ።