የመስቀል ደመራ በዓልና የግሸን ደብረ ከርቤ በዓላት ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲከበሩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውን የደሴ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡

123

ደሴ: መስከረም 05/2015 ዓ.ም (አሚኮ) መስከረም 16/2015 ዓ.ም በአደባባይ ለሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል እና መስከረም 21/2015 ዓ.ም ለሚከበረው የግሸን ደብረከርቤ ንግስ በዓል ወደ ከተማዋ የሚመጡ እንግዶችና ምእመናን ሃይማኖታዊ በዓላቱን ያለአንዳች የፀጥታ ችግር አክብረው ወደ አካባቢያቸው እንዲመለሱ ከፖሊስ፤ ከአድማ ብተና፤ ከፌደራል ፖሊስና ከሚሊሻ አባላት ጋር በቅንጅት እየተሠራ መኾኑን የደሴ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ማኅበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ዋና ክፍል ኀላፊ ምክትል ኮማንደር አበባው አሻግሬ ገልጸዋል፡፡
ምክትል ኮማንደር አበባው አሻግሬ ጥብቅ ክትትል የሚያስፈልጋቸው ሕዝቡ በብዛት የሚንቀሳቀስባቸውን ቦታዎች በስውር በተንቀሳቃሽና በቋሚ ጥበቃ የሚደረግባቸውን በመለየት የፀጥታ ችግር እንዳያጋጥም ግብረኀይል ተቋቁሞ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡
ከከተማው አሁናዊ የፀጥታ ሁኔታ አንፃር እስካሁን 119 ፀጉረ ልውጦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀው በሁሉም ኬላዎች ሰርጎገቦች ወደ ከተማዋ እንዳይገቡ ጥብቅ ፍተሻና ክትትል እየተደረገ መኾኑን አመላክተዋል፡፡ በከተማዋ የተቀመጡ ክልከላዎች እንዳይጣሱ ማኅበረሰቡን በማደራጀት ሕዝቡ ለሰላሙ ዘብ እንዲቆም ማድረግ ስለመቻሉም አንስተዋል፡፡
የደሴና አካባቢዋ ማኅበረሰብም የተለመደ እንግዳ ተቀባይነቱን በማረጋገጥ የከተማዋን ገጽታ የመገንባት ኀላፊነቱን እንዲወጣ የደሴ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ማኅበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ዋና ክፍል ኀላፊ ምክትል ኮማንደር አበባው አሻግሬ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ቤተልሄም ሰለሞን
ለሀገር ክብር በትግል እናብር!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

Previous article“ወልቃይት ጠገዴ የጎበዙን ሀገር ያሳደገኝ እኔ የማውቀው ልናገር”
Next article“በኢትዮጵያ የድንበርና ድንበር ተሻጋሪ የውኃ ሀብቶችን ጥቅም ላይ ለማዋል እየተሠራ ነው”የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ