
ባሕር ዳር፡ መስከረም ዐ4/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ አሸባሪው ሕወሃት ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ የሚያሳስትበትን የመረጃ ጦርነት በተሟላ የመረጃ ትንተና ማክሸፍ እንዳለባት በሞስኮ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ተመራማሪ ማቲው ኢህሬት ገልጸዋል፡፡
አሸባሪው ሕወሃት በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ክህደት ከፈፀመ በኋላ የሽብር ተግባሩን በማጠናከር በአማራና አፋር ክልሎች ወረራ በመፈጸም በንፁሃን ላይ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት አድርሷል፡፡
በንጹሃን ኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸመው ግፍ አልበቃ ብሎት ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት በመንግስት የተጠቃ በማስመሰል ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ እያደናገረ ይገኛል፡፡
መንግስት የዘረጋለትን የሰላም እጅ በማጠፍ ሶስተኛ ዙር ወረራ የጀመረው የሽብር ቡድኑ ዛሬም እንደ ትናንቱ ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማሳሳት የሀሰት ፕሮፖጋንዳ እየነዛ ነው፡፡
በሞስኮ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ተመራማሪ ማቲው ኢህሬት ለኢዜአ እንዳሉት፤ አሸባሪው ሕወሃት ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ የሚያደናግርበት መንገድ የመረጃ ጦርነትን በመጠቀም ነው፡፡
የሽብር ቡድኑን የተዛባ መረጃ በመቀበል ድጋፍ የሚያደርጉለት አንዳንድ ምዕራባውያንና የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን አመራሮች በተሟላ መረጃ መሞገት ይገባል ብለዋል፡፡
በመረጃ ጦርነት ውስጥ ተገቢ ትንተና በማድረግ የሌሎችን የተሳሳተ መረጃ ማክሸፍ ካልተቻለ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተዛባ ዕይታ መያዙ አይቀሬ ነው ይላሉ፡፡
በመሆኑም ኢትዮጵያ ብሎም አፍሪካውያን ያሉበትን ነባራዊ እውነታ ለዓለም ለማስተዋወቅና ተደማጭነታቸውን ለማሳደግ የመረጃ ጦርነትን ተንትኖ የማቅረብ ልምዳቸውን ማሳደግ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
የሰላም ብያኔ በሀገራት ብሔራዊ ጥቅም ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ኢትዮጵያም በመረጃ ጦርነት የፈራረሰችው ሶሪያን እጣ እንዳይገጥማት የተደራጀ የመረጃ ትንትና ስርዓት መዘርጋት እንዳለባት ጠቁመዋል፡፡
ምዕራባውያን ከኢትዮጵያ ይልቅ አሸባሪው ሕወሃትን የሚደግፉት እንደ ሀገር አቅም ያለው መንግስት እንዳይኖርና በአፍሪካ ቀንድና በቀጠናው ያላትን ተፅዕኖ ለማሳነስ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ያላት ተሰሚነት እንዳይጎላና የልማት ፕሮጀክቶችን በማሳካት ርሃብና ጦርነትን ለማጥፋት የጀመረችውን ጉዞ ለማደናቀፍ የታቀደ እኩይ ሴራ ነውም ብለዋል፡፡
የሽብር ቡድኑን በምርጫ ስልጣን ከያዘ መንግስት ጋር ማወዳደር ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ከመሆኑም ባለፈ፤ መሬት ላይ ያለውን እውነትና የአፍሪካ ህብረትን ጥረት መካድ ነው ብለዋል፡፡
ከኢትዮጵያ ይልቅ አሸባሪው ህወሓትን የመደገፍ አባዜ ኢትዮጵያን በብሔር ማንነትና በተለያዩ ቡድኖች በማጋጨት ወደ ትንንሽ ግዛቶች ከፋፍሎ እንደፈለጉ የማስተዳደር ፍላጎት መሆኑንም አንስተዋል፡፡
የሽብር ቡድኑ የጥፋት ዓላማውን ለማሳካት ህጻናትን ለጦርነት እየመለመለና እየማገደ እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሠራተኞችን እያገተ በዝምታ የሚያልፉ ኃይሎች መኖራቸውን በመጠቆም።
መንግስት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ባለበት ወቅትም የሽብር ቡድኑ ውጊያ ሲከፍትና በንጹሃን ላይ ጭፍጨፋ ሲፈጽም ዝም የሚሉትም ከጀርባ ማሳካት የሚፈልጉት ዓላማ ስላለ ነው ይላሉ።
ለሀገር ክብር በትግል እናብር‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J