“ተቆርቋሪ ትግራዊያን እልህ አሰጨራሽ ትግል አድረገዉ ሕዝባቸዉን ከአሸባሪው ሕወሃት ነጻ ማዉጣት ይገባቸዋል” የፖለቲካል ኢኮኖሚ ተንታኙ ሸዋፈራዉ ሽታሁን

124

አዲስ አበባ፡ መስከረም 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው ሕወሃት በትግራይ ሕዝብ ላይ የጫነው የመከራ ቀንበር የሚያሳስባቸው ትግራዊያን እልህ አሰጨራሽ ትግል አድረገዉ ሕዝባቸዉን ነጻ ማዉጣት ይገባቸዋል ሲሉ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ተንታኙ ሸዋፈራዉ ሽታሁን ተናግረዋል፡፡
የትግራይ ሕዝብ ነጻነቱን እንዲጎናጸፍ አሸባሪውን ቡድን ለመመከት በሚደረገው ጥረት ትግራውያን በባለቤትነት የነቃ ተሳትፎ ሊያደርጉ እንደሚገባ ነው የፖለቲካል ኢኮኖሚ ተንታኙ ሸዋፈራዉ የሚገልጹት፡፡
አቶ ሸዋፈራዉ ከጥንስስ እስከ ዉልደት፣ ከጉልምስና እስከ ሽምግልና ርህራሄን የማያውቀዉ እሳቤዉ እና ተግባሩ ክፋት እና ጥፋት ብቻ የኾነዉ አሸባሪዉ ሕወሃት ትናንት በስልጣን ላይ እያለም ኢትዮጵያዊያንን በማር የተለወሰ መርዝ ሲያጠጣ ብዙዎች ከእንቅልፋቸው የነቁት አርፍደው እንደነበር ነው ያስረዱት፡፡
ይህ አሸባሪ ቡድን አሁንም ከስልጣን ወርዶ የተዋረሰዉ ሰይጣናዊ ባህሪ አለቀዉ ብሎ ኢትዮጵያዊያንን ሰላም እየነሳ ይገኛል፡፡
የፖለቲካል ኢኮኖሚ ተንታኙ አቶ ሸዋፈራዉ እንዳሉት “አሸባሪው ሕወሃት አይደለም ለሌሎች ኢትዮጵያዊን በስሙ ለሚነግድበት የትግራይ ሕዝብም የጭቃ ቁስል ነዉ፡፡ የትግራይ እናቶች የወላድ መካን ኾነዋል ነው ያሉት፡፡ ሕዝቡ ይህን ያክል መከራ የተጋረጠበት ተማርን የሚሉት ወጣት ትግራዊያን እልህ አሰጨራሽ ትግል አድርገዉ አሸባሪውን ሕወሓት ከሕዝባቸው ጫንቃ ላይ አላቀው ነፃ ማዉጣት እየቻሉ ባለማድረጋቸው ነው” ይላሉ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ተንታኙ ፡፡

እንደ አቶ ሽዋፈራዉ ማብራርያ፤ ሕወሃት አሁን በከፈተዉ ጦርነት መላ ትግራዊያንን እያሰለፈ እና እያስጨረሰ ያለዉ የትግራይን ማንነት የሚቀማ ኃይል እየመጣበት እንደኾነ በማስመሰል በሚነዛው ፕሮፖጋንዳ እንደኾነ ነው የገለጹት፡፡ በመኾኑም የሽብር ቡድኑን እኩይ ተግባር የሚያመክን የመረጃ ጦርነት በስፋት ሊተገበር ይገባል ነው ያሉት፡፡
ከትናንት እስከ ዛሬ የትግራይ ሕዝብ ኅልዉና ያለ እሱ ምንም እንደኾነ እየሰበከ እድሜዉን ለማራዘም እየተፈራገጠ ነዉ የሚሉት አቶ ሽዋፈራዉ፤ እዉነታዉ ግን የትግራይ ሕዝብ የነጻነት ጮራ የሚፈነጥቀዉ የዚህ ሰው -በላ ቡድን በሕዝቡ ተቀባይነትን ሲያጣ እንደኾነ ነው የሚገልጹት፡፡ ለዚህም ትግል የትግራይ ሕዝብ የነቃ ተሳትፎ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- በለጠ ታረቀኝ
ለሀገር ክብር በትግል እናብር‼

Previous article“ወታደር መሆን ከራስ በፊት ለሕዝብ ጥቅም እና ለሀገር ክብር መቆም ነው” መቶ አለቃ እውነቱ ማዘንጊያ
Next articleMaxxansa gaazexaa Hirkoo Hagayya 30/2014