አግራ በአፍሪካ የምግብ ዋስትና ችግርን ለመዋጋት የ550 ሚሊዮን ዶላር ፈንድ ይፋ አደረገ።

180

ባሕር ዳር: መስከረም 03/2015 ዓ.ም (አሚኮ) “ቅንጅት ለአፍሪካ የአረንጓደ አብዮት” (አግራ) የተሰኘው ድርጅት አህጉሪቱ የራሷን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ለምታደርገው ጥረት 550 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚሆን የማስጀመሪያ ፈንድ ይፋ አደረገ።
በቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የቦርድ ሊቀመንበርነት የሚመራው “ቅንጅት ለአፍሪካ የአረንጓደ አብዮት” (አግራ) የተሰኘው የበጎ አድራጎት ድርጅት ትናንት ይፋ እንዳደረገው፥ በ15 የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ 28 ሚሊዮን አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዷል።
በአዲሱ ፖሊሲ መሰረት ድርጅቱ የግብርና ምርታማነትን እና ገቢን ለማሳደግ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራም ተመላክቷል።
ድርጅቱ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ዋነኛ ትኩረቱ የዘር አጠቃቀም ስርዓትን በማሻሻል፣ የመንግስት ተሳትፎን በማሳደግ፣ የግብርና ግብዓት አቅርቦት ሰንሰለት እና የአየር ንብረት ለውጥ ችግሮችን በመቅረፍ ላይ እንደሚሰራም ነው የተገለፀው፡፡
የአየር ንብረት ለውጥ እና እንደ ማዳበሪያ ያሉ የግብርና ግብዓቶች ዋጋ መናርን ጨምሮ በቀጠናው ያሉ አነስተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ አርሶ አደሮች ወቅታዊውን የውጭ ጫና ተሸክመው እንደሚገኙም የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
በብዙ ልፋት የተገኙ የግብርና ውጤቶች አሁን ላይ በውጫዊ ክስተቶች በተለይም በአየር ንብረት ለውጥ ተፅእኖ ምክንያት ስጋት ውስጥ በመሆናቸው ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ መንቀሳቀስ እንደሚገባ ነው የተጠቆመው።
የአግራ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በምሥራቅ አፍሪካ በየወቅቱ የሚከሰተው ድርቅ እንዲሁም በደቡባዊ አፍሪካ የሚታየው ሃያል አውሎ ንፋስ አሉታዊ ተፅእኖ ማስከተላቸውን ገልጸዋል።
የአየር ሁኔታ እና የአየር ንብረት ለውጥ ችግሮች እንዲሁ ከግብርና ግብዓቶች የዋጋ መናር ጋር ተዳምረው በግብርና ምርትና ምርታመነት ላይ እያስከተሉ ያሉት ተጽዕኖ በቀላሉ የሚታይ እንዳልሆነም መናገራቸውን የቦርዱን ሊቀመንበር ጠቅሶ ዘ ኢስት አፍሪካ ዘግቧል።
ለሀገር ክብር በትግል እናብር!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

Previous article“ከወልቃይት ሠማይ ሥር፣ ከተከዜ ወንዝ ዳር”
Next articleየኢትዮጵያን ባሕልና የአማርኛ ቋንቋ እንደሚያስተዋውቁ የተለያዩ የውጭ ሀገራት ዜጎች ገለጹ።