“በርካታ የትግራይ ክልል ልጆች እያለቁ ነው” በምዕራብ ግንባር እጃቸውን የሰጡ የሽብር ቡድኑ እኩይ ድርጊት ፈፃሚወች

415

ባሕር ዳር፡ መስከረም 03/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ለአሸባሪው ሕወሃት ሲዋጉ በምዕራብ ግንባር እጃቸውን የሰጡ የሽብር ቡድኑ እኩይ ድርጊት ፈፃሚወች የትግራይ ክልል ወጣቶች ስለ አስከፊው ጦርነትና ከተያዙ በኋላ በመከላከያ ሰራዊት ስለተደረገላቸው አያያዝ ተናግረዋል።
ለቤተሰቧ የመጀመሪያ ልጅ የሆነችው አፀደ ወልደ ሚካኤል፣ የሽብር ቡድኑ አሸባሪው ሕወሃት እኩይ ድርጊት ፈፃሚወች በርካታ የትግራይ ክልል ወጣቶች ማለቃቸውን ተናግራለች።
ሌላኛዋ፣ የ16 አመቷ መርሀዊት ግደይ ስልጠና ወስዳ መግባቷን ገልፃ በነበረው ጦርነት አስቸጋሪ ጊዜያትን አሳልፋለች ።
ውጊያው አስከፊ መሆኑን የሚገልፁት ምርኮኞቹ፣ የአሸባሪው ሕወሃት አመራሮች ለራሳቸው ስልጣን እንጂ ለትግራይ ልጆች እያሰቡም ብለዋል።
ኢቢሲ እንደዘገበው፤ በጦርነት እየተሳተፉ የሚገኙ “የአሸባሪው ሕወሃት ፕሮፖጋንዳ ሰለባዎች እጃችሁን ለመከላከል ሰራዊት ስጡ” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ለሀገር ክብር በትግል እናብር‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

Previous articleበኩር ጋዜጣ – መስከረም 02/2015 ዓ.ም ዕትም
Next articleበአንዳንድ ምዕራባውያን ዒላማ ውስጥ የገቡ ቀደምት ልዕለ ኃያላን ሀገራት!