
ባሕር ዳር: ጳጉሜን 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) “የኢትዮጵያ አየር ኃይል የጥንካሬ ምንጭ አንድነት ነው፤ አንድነታችንን ይበልጥ በማጠናከር የትኛውንም አይነት ጥቃት በብቃት ለመመከት ዝግጁ ነን” ሲሉ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ተናገሩ፡፡
የኢትዮጵያ አየር ኃይል የአንድነት ቀንን በተለያዩ መርሐግብሮች አክብሯል።
በመርሐግብሩ የኢትዮጵያ አየር ኀይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ፣የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባና ሌሎች እንግዶች የታደሙ ሲሆን ከፍተኛ መኮንኖች ማዕረግ የማልበስ፣ የአየር ኀይል ሠራተኛ ቤተሰቦች ድጋፍ ማድረግና የእውቅና መርሐግብር ተከናወኗል፡፡
የኢትዮጵያ አየር ኀይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት በ2014 ዓ.ም አየር በኢትዮጵያ ህልውና ላይ ተደቅኖ የነበረውን አደጋ በመመከት ረገድ ደማቅ ታሪክ መጻፉን ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያን አየር ክልል በመጣስ ለአሸባሪው ህወሃት መሳሪያ ለማቀበል የሞከረ የጦር አውሮፕላን ላይ የተወሰደውን እርምጃም ለአብነት አንስተዋል፡፡
የኢትዮጵያን ህልውናና ሉዓላዊነት በማስጠበቅ ረገድ የአየር ኃይል አባላት ከፍተኛ ጀብዱ መፈጸማቸውንም አብራርተዋል፡፡
“የኢትዮጵያ አየር ኃይል የጥንካሬ ምንጭ አንድነት ነው” ያሉት ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ፤ በቀጣይም አንድነታችንን በማጠናከር የአየር ክልላችንን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ ከመቸውም ጊዜ በላይ ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡
በአየር ኃይሉ ላይ የተከነወነው የሪፎርም ስራ ውጤታማ እንደነበር ጠቅሰው፤ አየር ኃይሉ ለአገር ሉዓላዊነት አስተማማኝ ዘብ የሚያደርገውን ትልቅ ራእይ ሰንቆ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ዘገባው የኢዜአ ነው
ለሀገር ክብር በትግል እናብር!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J