
ባሕር ዳር፡ ጳጉሜን 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በመላው አሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በአዲሱ ዓመት ለሀገራቸው እያደረጉት ያለውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ አምባሳደር ስለሺ በቀለ ጠየቁ።
በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ስለሺ በቀለ፤ በመላው አሜሪካ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን የ2015 ዓ.ም አዲስ ዓመትን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አምባሳደሩ በመልካም ምኞት መልዕክታቸው “በመላው አሜሪካ የምትኖሩ ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንኳን ለ2015 ዓ.ም አዲስ ዓመት አደረሳችሁ” ብለዋል፡፡
“ዓመቱ የሰላም፣ የፍቅር እና የአንድነት እንዲሆን ልባዊ ምኞቴን እየገለጽኩ ለአገራችሁ እያደረጋችሁ ያላችሁትን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ከአደራ ጭምር እጠይቃለሁ” ብለዋል፡፡
ለሀገር ክብር በትግል እናብር‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J