ግንባር ድረስ የዘለቀው ደጀንነት!!

154

ባሕር ዳር፡ ጳጉሜን 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ወይዘሮ ደስታ ጌታሁን ይባላሉ፡፡በሰቆጣ ከተማ በትንሽዬ የዳስ ውስጥ ቡና እና ሻይ በመሥራት በሚያገኙት ገቢ ሁለት ልጆቻቸውን ያሳድጋሉ፡፡
ወይዘሮ ደስታ ለእናት ሃገሩ ኢትዮጵያ ለሚፋለመው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ያላውን ደጀንነት ከእለት ጉርሳቸው በማካፈል አሳይተዋል። ከልጆቻቸው እና ከራሳቸው የእለት ጉርስ ቀንሰው በግዳጅ ቀጠናው ለሚፋለሙ የሰራዊት አባላት ቡና እና ሻይ ይዘው ተገኝተዋል፡፡
ወይዘሮ ደስታ ጌታሁን ሰራዊቱ በግዳጅ ላይ ፋታ ሲያገኙ ቡና እና ሻይ በማቅረብ ደጀንነታቸውን በጀግንነት አስመስክረዋል፡፡ መረጃው የመከላከያ ሰራዊት ነው።
ለሀገር ክብር በትግል እናብር‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

Previous article“በማይካድራው ጭፍጨፋ ወቅት በዓይኔ ያየሁት የአማራ ሕዝብ ብዙ ተገድሏል” የሕወሃት ታጣቂ ምርኮኛ
Next article“2014 ዓ.ም የአሸባሪው ሕወሃት ወረራን በመመከት የኢኮኖሚ ጫናውን ለመቋቋም ጥረት የተደረገበት ነበር” ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)