
ባሕር ዳር፡ ጳጉሜን 01/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ዳያስፖራዎች በአካልና በዲጂታል ሚዲያው ድምጻችሁን ማሰማት እንድትቀጥሉ ከአደራ ጭምር እጠይቃለሁ ሲሉ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ስለሺ በቀለ
ጥሪ አቅርበዋል።
በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው እንዲሁም ከሌሎች የአሜሪካ ግዛቶች ወደ ዲሲ በመሰባሰብ የህወሃትን ሶስተኛ ዙር ወረራ እና የተቀናጀ የሃሰት ፕሮፖጋንዳ በመቃወም፤ በኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለውን ገደብ የለሽ ያልተገባ ጫና፣ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ድምጻችሁን ላሰማችሁ ዳያስፖራ ወገኖች ሁሉ ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል አምባሳደሩ።
አንድነታችን እና ሉዓላዊነታችን ለመናድ እየተደረገብን ያለው ሁሉን አቀፍ የእጅ ጥምዘዛ እና የሃስት የሚዲያ ዘመቻ እስኪቆም ድረስ በአካልና በዲጂታል ሚዲያው ድምጻችሁን ማሰማት እንድትቀጥሉ ከአደራ ጭምር እጠይቃለሁ ሲሉ አምባሳደር ስለሺ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
ለሀገር ክብር በትግል እናብር‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J