
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 30/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ልዩ ስሙ ወለህ በሚባል አከባቢ 10 ንጹሀን ዜጎችን በግፍ ጨፍጭፏል።
ወይዘሮ ለምለም አዳነ ሰቆጣ ወረዳ ልዩ ስሙ ወለህ ማርያም ቀበሌ ነዋሪ ነበሩ፤ ልጆቻቸውን ለማሳደግ፣ ለማስተማርና ከቁም ነገር ለማድረስ ደፋቀና ሲሉ የነበሩ እናት ናቸው።
ንጹሀንን መጨፍጨፍ መገለጫው የኾነው አሸባሪው የህወሃት ቡድን ወይዘሮ ለምለም አዳነን ከነልጆቻቸው ቤታቸው ውስጥ በነበሩበት ከባድ መሳሪያ በመተኮስ በግፍ ጨፍጭፏቸዋል።
በጭፍጨፋው የተገደሉት ሰባቱ የቤተሰቡ አባላት ናቸው። 3ቱ ደግሞ ተፈናቃዮች ናቸው።
የሰላም ድርድሩን ረግጦ በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ያወጀው ይህ የሽብር ቡድን በቤታቸው የተቀመጡትንና ነፍጥ ያላነገቱትን ንጹሀን ሴትና ህጻናትን ነው በከባድ መሳርያ የጨፈጨፋቸው።
አሸባሪ እና አውዳሚ ቡድኑ ከሰላም ይልቅ ጦርነትን የመረጠው የሀገሪቷ ዜግች በሰላም እንዳይኖሩ የወጠነው የክፋት መንገድ መሆኑን ነው ይህ ዘግናኝ ጭፍጨፋ የሚያሳየው።
መረጃው የዋግኽምራ ኮሙኒኬሽን ነው።
ለሀገር ክብር በትግል እናብር‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J