
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ.ር) በማሕበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ አሸባሪው ህወሓት ለትግራይ ሕዝብ የሚቀርብን ሰብአዊ ዕርዳታን ለጦርነት ማዋል ሕዝቡን መከራ ውስጥ ከቶታል ብለዋል።
አሸባሪዉ ህወሓት ለትግራይ ሕዝብ የሚቀርብን ሰብአዊ ዕርዳታን ለጦርነት ማዋል የጀመረው ዛሬ ሳይሆን ከምስረታው ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡
በ1977 ዓ.ም በነበረው ረሀብ ለሕዝቡ የተላከውን ምግብ ሽጦ ጦር መሳሪያ የገዛው ይኸው ህወሓት የሚባል አሸባሪ ድርጅት ነው፡፡
ህወሓት አሁንም ይህንን ባህሪውን ቀጥሎበት የትግራይን ሕዝብ መከራ እያራዘመ ነው፡፡ የትግራይ ሕዝብ መሰረታዊ ጠላት ህወሓት እንጂ የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግስት አይደሉም፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግስት ለትግራይ ሕዝብ ዕርዳታ እያቀረቡ እና ከትግራይ ክልል ወደ አፋርና አማራ ክልሎች የሚፈልሱ የትግራይ ተወላጆችን በኢትዮጵያዊ ጨዋነት እየተቀበሉ እያስተናገዱ ነው፡፡
በአንፃሩ ህወሓት ለሕዝቡ የተላከውን ዕርዳታ በመዝረፍ ለጦርነት እየተጠቀመበት ነው፡፡ ይህም ህወሓት የትግራይ ሕዝብ መሰረታዊ ጠላት መሆኑን በተጨባጭ ያሳያል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J