በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ ላይ ከጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተሰጠ መግለጫ!

138

አሸባሪው ህወሓት የመንግስትን የሰላም አማራጭ ወደ ጎን በመተው ዳግም ጦርነት ማወጁ ለሰላም ቦታ የማይሰጥ መሆኑን ማረጋገጫ ነው።

ቡድኑ ኢትዮጵያን ለማፍረስና ለመበታተን ወደ ኋላ እንደማይል በግልጽና በአደባባይ ያሳየበት ነው።

በሰሜን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት መንግስት የጀመረውን የሰላም አማራጭ በመተው አሸባሪው ህወሃት ሰላም እንደማይፈልግ አረጋግጧል።

በቅርቡም በጋምቤላ ከተማ በተላላኪዎቹ በጋ.ነ.ግ እና በሸኔ የሽብር ቡድኖች ሊደርስ የነበረውን የከፋ ጥቃት በፀጥታ ሀይሉ እና በህብረተሰቡ የተቀናጀ ጥረት ማክሸፍ ተችሏል።

አሸባሪ ቡድኑ በተለይም የትግራይ ክልል ወጣቶችና አጠቃላይ ህዝቡን ለማያባራ እልቂትና የከፋ ችግር በመዳረግ የራሱን ህልውና ለማስቀጠል እየሰራ ይገኛል።

በተለያዩ አጋጣሚዎች ሰላም ወዳድ በመምሰል የሚያሰራጨው መረጃ ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማሳሳት የሚጠቀምበት ስልቱ ነው።

አሁን ላይ የመንግስትን የሰላም አማራጭ ባለመቀበል ጦርነት መክፈቱ የቡድኑን አረመኔያዊነት ያመላክታል።

ወገናችን የሆነው የትግራይ ህዝብ የሰላም አማራጭን ባለመቀበል ዳግም ጦርነት የከፈተውን ቡድን በአንድነት ሊያወግዘውና ሊቃወመው ይገባል።

አሸባሪው ህውሃት ዳግም በከፈተው ጦርነት ሳንሸበር የአንድነትና የመተሳሰብ እሴታችን ይበልጥ ማጠናከር ይኖርብናል።

የዜጎች ደህንነትን ለመጠበቅ ሲል የፌደራል መንግስት የሚወሰደዉን ህጋዊ እርምጃዎችን በፅኑ የሚደግፍ መሆኑን የጋምቤላ ህዝቦች ብሐራዊ ክልላዊ መንግስት ያረጋግጣል።

የሽብር ቡድኑ የከፈተውን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መንግስት የሚያደርገውን ጥረት የጋምቤላ ክልል ህዝብና መንግስት የሚያደንቅ ሲሆን ከኢትዮጵያዊያን ወገኖቹ ጋር በመሆን የሚጠበቅበትን ይወጣል።

የጋምቤላ ህዝቦች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት
ነሐሴ 22/2014 ዓ.ም
ጋምቤላ

Previous articleየቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ህወሓት በአማራ እና አፋር ክልሎች የጀመረውን ወረራ ለመቀልበስና የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር ዝግጁ መሆኑን አረጋገጠ።
Next articleʺ ኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረጉ ነው” የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዲያቆን ተስፋው ባታብል