ለአሸባሪው ህወሃት የጦር መሳሪያ ጭኖ የኢትዮጵያ የአየር ክልል ጥሶ የገባ አውሮፕላን በአየር ኃይል መመታቱ ተገለጸ።

1003

ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 18/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያን መዳከም የሚፈልጉና ለዚሁም ለዘመናት የሚንቀሳቀሱ ህወሃትን በመደገፍ ላይ የሚገኙ ታሪካዊ ጠላቶች ንብረት እንደሆነ የሚታመን አውሮፕላን ለሽብር ቡድኑ የጦር መሳሪያ ጭኖ በሱዳን አልፎ የኢትዮጵያን አየር ክልል ጥሶ ሲገባ በጀግናው አየር ሃይል ተመትቶ ወድቋል።

ሠራዊቱ የሀገሩን ሉዓላዊነት ለማስከበር ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ ዝግጁ መኾኑም ተገልጿል።

በሀገር መከላከያ ሠራዊት የመከላከያ ህብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ የመከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊ ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ላለፉት በርካታ ወራት ከፍኛ ወታደራዊ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየው አሸባሪው ህወሃት ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ ኃይሉን ለውጊያ ሲያስጠጋ ነበር።

በየጊዜውም ተኩስ እየከፈተ የሀገር መከላከያን ሲተነኩስ መቆየቱንም ነው ያነሱት።

ቡድኑ መንግስት የዘረጋውን የሰላም አማራጭ ከቁብ ሳይቆጥርና የሰላም ሂደቱ ቴክኒካሊ ፈርሷል ብሎ መግለጫ ባወጣ ማግስት ነሐሴ 17 ቀን 2014 ዓ.ም ሌሊት 11 ሰዓት ላይ በቆቦ ግራና ቀኝ ባሉ አካባቢዎች፣ በዞብል ተራራ፣ በቢሶበርና በወትወት ውጊያ መክፈቱን ገልጸዋል።

በዚህም የተኩስ አቁም ስምምነቱን ማፍረሱን ጠቅሰው፤ የሽብር ቡድኑ እየላከ ያለው ጀሌ በሀገር መከላከያ ሠራዊትና በጸጥታ ኀይል እየተለበለበ ነው ብለዋል።

ሜጀር ጀኔራሉ አክለውም በሱዳን አድርጎ የአየር ክልላችንን ጥሶ በሁመራ ሰሜናዊ ክፍል በኩል ወደ ትግራይ ሊያልፍ የነበረና ለሽብር ቡድኑ የጦር መሳሪያ ሊያቀበል የነበረ ንብረትነቱ የማን እንደኾነ ያልታወቀ አውፕላንም በጀግናው አየር ሃይል ሌሊት አራት ሰዓት ላይ ተመትቶ መውደቁን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስደፈር የሽብር ቡድኑን እየጋለቡ ያሉ ኀይሎች ቢኖሩም የሀገር መከላከያ ሠራዊትና ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን ለማስክበር በተጠንቀቅ ላይ ምኾናቸውን ጠቅሰዋል።

በቀጣይም የሽብር ቡድን ሀገር የማፍረስ ህልሙን ትቶ ወደ ሰላማዊ መፍትሔ ካልመጣ እስከመጨረሻው ርምጃ ለመውሰድ ሙሉ ዝግጅት መደረጉን ጠቅሰዋል።

አሁን የመከላከል ርምጃ እየተወሰደ ሲሆን በቀጣይም የማጥቃት ርምጃዎች እንደሚኖሩ ነው የጠቀሱት።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼

ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

Previous articleየመከላከያ ሠራዊትን ወቅታዊ ሁኔታ፣ ባልተረጋገጡ፣ ባልተገቡ መረጃዎችና አሉባልታዎች የመዘገብ ወይም የማራገብ አሉታዊ ሙከራዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙ መከላከያ ሚኒስቴር አሳሰበ።
Next articleʺ የተባበሩ ክንዶች ያስከብራሉ፣ አንድ የኾኑ ጀግኖች ድል ይቀዳጃሉ”