በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት የደረሰበት የሰቆጣ ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት በተሻለ የጥራት ደረጃ መልሶ ሊገነባ ነው።

173

ሰቆጣ: ነሐሤ 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት የደረሰበት የሰቆጣ ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት በተሻለ ደረጃ መልሶ ለመገንባት የሚያስችል የመሰረት ድንጋይ ዛሬ ተቀምጧል።
በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው የመሰረት ድንጋዩን ያስቀመጡት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮነን፣ ትምሕርት ሚኒሥትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ናቸው።
የትምሕርት ሚኒሥትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የሰቆጣ ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት የመልሶ ግንባታ ሥራ በቅርብ ቀን ይጀመራል ብለዋል። ትምሕርት ቤቱ በፊት በነበረበት ደረጃ ሳይኾን በተሻለ ደረጃ ተገንብቶ በ2015 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ ለአገልግሎት እንደሚደርስ ገልጸዋል።
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) የትምሕርት ቤቱ ግንባታ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የክልሉ መንግሥት የሚጠበቅበትን ሁሉ ድጋፍና ትብብር እንደሚያደርግ ተናግረዋል። የፈረሰውን ትምሕርት ቤት በተሻለ ደረጃ መልሶ ለመገንባት ትምሕርት ሚኒስቴር ላደረገው እንቅስቃሴም ምስጋና አቅርበዋል።
ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

Previous article“ቺርቤዋ ናሲ 15 ጌርክ 2014 ም.አ እትሜት”
Next articleአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) ባለፉት ሦሰት ዓመታት ከ3 ቢሊዮን 478 ሚሊዮን ብር በላይ በኾነ ወጭ 650 የሚጠጉ ፕሮጀክቶችን ማከናወኑን ገለጸ፡፡