215

በእንግሊዟ ንግሥት አድናቆት የተቸረውን የጢስ አባይ ፏፏቴ ድንቅ ሥፍራ ይጎብኙ!!

👉የአባይ ወንዝ የሚፈጥረው የጢስ አባይ ፏፏቴ ቀልብን የሚስብ ነው፡፡

👉የጢስ አባይ ፏፏቴ ከባሕር ዳር ምስራቃዊ አቅጣጫ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት በጢስ አባይ ከተማ ይገኛል፡፡

👉ፏፏቴው አራት መቶ ሜትር ስፋት ሲኖረው 45 ሜትር ወደታች ርቀት ባለው ገደል ውስጥ ተወርውሮ ይገባል፡፡

👉የአባይ ውሃ ወደ ጥልቁ ገደል ሲወረወር ማራኪ የነጎድጓድ ድምፅ ይፈጥራል፤ አካባቢውን እንደ ጢስ የሚሸፍን የውሃ ብናኝ እና ህብረ ቀለማትን ይፈነጥቃል።

👉በተወሰነ ጊዜ ልዩነትም ብልጭ እያለ የሚጠፋ ቀስተ ደመናም ይፈጥራል።

👉ወደ ፏፏቴው ለመሄድ ሁለት አማራጮችን መጠቀም ይቻላል፦

👉አንደኛው አማራጭ ከከተማዋ 1 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትሮችን ያክል በመኪና ከተጓዙ በኋላ ቁልቁለት እና አቀበት የኾነውን የእግር መንገድ ለ20 ደቂቃ ተጉዘው ፏፏቴው ጋር መድረስ ይቻላል።

👉በዚሁ አማራጭ ከሄዱ በ17ኛው ክፍለ ዘመን በአፄ ሱስንዮስ ዘመነ መንግስት እንደተሰራ የሚነገርለትን የአላታ ድልድይን ማየት ይችላሉ እረፍትም ያደርጋሉ።

👉ሁለተኛው አማራጭ እጅግ አስደሳች ሲኾን እዚያው ወንዙ አካባቢ በሚሰራ “ታንኳ” ወይም ጀልባ በመጠቀም እዚያው ፏፏቴው ድረስ መሄድ ይቻላል።

👉በታሪክ አጋጣሚ የእንግሊዟ ንግስት ኤልሳቤት ሁለተኛ በፈረንጆቹ 1965 ኢትዮጵያን ሲጎበኙ ጢስ አባይ ፏፏቴንም እንደተመለከቱ ታሪክ ያስረዳል፡፡

👉ከ50 ዓመታት በላይ በቱሪዝም መስህብነት እያገለገለ የሚገኘው የጢስ አባይ ፏፏቴ በ2ዐዐ7 ብቻ ከ1 ሚሊዮን ብር ላይ ለመንግስት ገቢ አስገኝቷል፡፡

👉የጢስ አባይ ፏፏቴን በማልማት ኢኮኖሚን በማይናወጥ መሰረት ላይ እንገንባ፡፡

የእረፍት ጊዜዎንም በጢስ አባይ ፏፏቴ ያሳልፉ!!

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼

ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleእንኳን ለበዓለ ደብረ ታቦር አደረሳችሁ!! “ዶሮ ከጮኽ የለም ሌሊት ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት”
Next article“ወጣቶች የኢትዮጵያን መፃዒ ተስፋ ለማበላሸት የሚሠሩ ኀይሎችን ሴራ በመታገልና አብሮነትን በማጽናት በሀገር ግንባታ ሂደት ላይ ንቁ ተሳትፎ ሊያደርጉ ይገባል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)