“አሸንድየ፣ ሻደይና ሶለል በዓልን ጠብቆ ማቆየት የሁሉም ኀላፊነት ነው” የአማራ ክልል ሴቶች ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኀላፊ ወይዘሮ አስናቁ ደረስ

199

ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 12/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሴቶች ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ አስናቁ ደረስ ሃይማኖታዊና ባሕላዊ መነሻና ትርጉም ላለው ለአሸንድየ፣ ሻደይና ሶለል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ኀላፊዋ አሸንድየ፣ ሻደይና ሶለል በዓል ከሕፃን እስከ አዋቂ ያሉ ሴቶች በነፃነት የሚታዩበት፣ በነፃነት ነግሠው የበዓሉ መገለጫ በኾኑ አልባሳትና ማጌጫዎች ተውበው ከነሐሴ ወር አጋማሽ ጀምሮ የሚያከብሩትና በጉጉት የሚጠብቁት የነፃነት ባሕላቸው መኾኑን ተናግረዋል፡፡
በዓሉ ቀልብን የሚስቡ ክዋኔዎች የሚከወኑበት በመኾኑ ለክልሉ ያለው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ከፍተኛ መኾኑን ነው ያስረዱት፡፡
ቢሮ ኀላፊዋ ይህን ታላቅ ሃይማኖታዊና ባህላዊ መሰረት ያለውን በዓል ጠብቆ ማቆየት የሁሉም ኀላፊነት መኾኑን ገልጸው ለባሕሉ ዋነኛ ባለቤቶች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ መረጃው የሴቶች ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየፌዴሬሽን ምክር ቤት 12ኛ ክልል እንዲቋቋም የሚያስችል ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ወሰነ።
Next articleሻደይ -የዋግሹሞቹ ሌላኛው ቀለም።