
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 12/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ስለሺ በቀለ ከኢትዮ-አሜሪካ የንግድ ዘርፍ ማህበር የቦርድ አባላት ጋር በአገራዊና የቢዝነስ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
አምባሳደር ስለሺ በውይይቱ ላይ በኢትዮጵያ ተግባራዊ እየተደረገ ስላለው የሪፎርም ሥራ አብራርተዋል፡፡
ኢትዮጵያ በአጎዋ የገበያ እድል እንደገና ተጠቃሚ እንድትኾን እየተሠሩ ያሉ ሥራዎችን አስረድተዋል፡፡
በቀጣይ የንግድ ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ኩባንያዎችን ከአሜሪካ ድርጅቶች ጋር የማስተሳሰር ሥራ እንዲሠራ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
እንዲኹም በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ንግድና ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ በጋራ ለመሥራት መግባባት ላይ መደረሱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
